በቀጣይ የህገመንግስት ማሻሻያ እንደሚኖር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) አስታወቁ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።
በዚህ ወቅት ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆኑ ተሹመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ (ዶ/ር) ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር በሀገራዊ ምክክሩ ምክረ ሐሳቦች መሠረት የሕገመንግስት ማሻሻያ እንደሚደረግ አሳውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የጠላቶቿን እኩይ ተግባርና የሚደቀኑባትን ተግዳሮቶች በብቃት ለመመከት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጓን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በምርጫው ለተሳተፉ 54 ሚሊዮን ዜጎች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ሂደቱም በብዙ መልኩ ትርጉም ያለው እንደነበር አስታውሰዋል።
"ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ የዴሞክራሲ ባህልም የሚፈተነው በምርጫ ወቅት ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕዝቡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ሕልውናውን ለማጽናት ድምፅ መስጠቱ የዴሞክራሲያዊ ባህላችን መሰረት እየጠነከረ መምጣቱን በግልጽ ያሳየ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በማንኛውም ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሸናፊና ተሸናፊ ሊሆኑ ቢችሉም "ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ የላትም" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሀገራዊ ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች በፍጥነት እየተለዋወጡና ኢ ተገማች እየሆኑ መምጣታቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም አስቀድሞ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች ቀደም ሲል ዝግጁ ባለመሆኗ ከፍተኛ ዋጋ መክፈሏን አስታውሰው አሁን ግን ካለፉት ስህተቶቿ በመማር ተግዳሮቶችን ለመመከት የሚያስችል ዝግጅት ማድረጓን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በቀጠናው ላይ ውሳኔ ሰጪነቷን በጉልበቷ የምታረጋግጥ መሆኗንና ይህንንም ያለማንም እገዛ እንደምታከናውን በመግለጽ የተያዘውን መዳረሻ ለማሳካት በሚገጥሙ እንቅፋቶች ሳትወድቅ ጉዞዋን እንደምትቀጥል ጠቁመዋል።
በውጭ ተጽዕኖ ስር ሳይወድቁ በሀገር በቀል ጥበብ ለመመራት የሚከለክል ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ጠ/ሚ ዐቢይ ሀገር ለዘመናት በመጤ ስልትና ባህል ማለፏንና ተጽዕኖዎችን ለመቆጣጠር አቋራጭ መንገዶች ሲወሰዱ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ሆኖም ኢትዮጵያዊነት ሊቀጥል የቻለው በመደመር እሳቤ እንደነበርና አሁንም የሚያዋጣው መንገድ ይኸው መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም ለነገ የምንሻገርበት የታሪክ አተያይ መስተካከሉን ጠቅሰው የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ስርዓት ከአንድ ዘርፍ ጥገኝነት ወጥቶ የብዝኃ-ዘርፍ ማቀናጀትና መተግበር ላይ ያተኮረ እንዲሆን መደረጉን ገልጸዋል።
ጠንካራ ቁጥጥርና ክትትል ያለበት የበጀት አካሄድን እንደሚከተሉም ያነሱ ሲሆን ለህብረ ብሔራዊ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ወሳኝ የሆነው የውል ትርክት ተገቢውን ትኩረት ያገኛል ብለዋል።
ምርታማነት ባህልና ሥርዓትም እንዲሆን የሚሰራ ሲሆን የሰላም ሁኔታዎችን የበለጠ ለማፅናት የውይይትንና የይቅርታን መንገድ እንደሚከተሉም ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የተጠናከረ የፀጥታና የደህንነት ዝግጁነት፣ ክትትል እንዲሁም ስምሪት ይኖረናል ሲሉ ተናግረዋል።
ሙስናን፣ ሌብነትን፣ የዘመድ አሰራርንና ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግሥት መረር ያሉ እርምጃዎችን እንደሚወስድም አስታውቀዋል።
በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

1 day ago