Logo
TIKVAH-SPORT
ሮናልዶ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ይመለሳል ?

የፖርቹጋል እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፔድሮ ፕሮኣንካ ሮናልዶ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ይመለሳል የሚል ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

ፕሬዝዳንቱ በሮናልዶ እና አሰልጣኙ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

“ ሮናልዶ የፖርቹጋል ትልቁ ምልክት ነው ” ያሉት ፕሬዝዳንቱ “ ለእሱ ክብር ሊሰጥ ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

አክለውም “ እሱ በቡድኑ ያለው ባለው ስፖርታዊ አቅም ምክንያት ነው ይሄ ሊያከራክር አይገባም "ብለዋል።

" የቴክኒክ ብቃቱ እስካለ ድረስ ሁልጊዜ የብሔራዊ ቡድኑ አካል ሆኖ ይቀጥላል እሱ ስሜታችን ይሄ መሆኑን ያውቃል “ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።

በቀጣይ ከሮናልዶ ጋር ቁጭ ብለው በመነጋገር መፍትሔ እንደሚፈልጉ ፕሬዝዳንቱ ጨምረው አሳውቀዋል።

@tikvahethsport      kidusyoftahe “ ሮናልዶ ስለ ቆይታው በራሱ ይወስናል ” ጆርጅ ጄሱስ “ ለመፍታት ቀላል ነገር ነው የተፈጠረው " የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጆርጅ ጄሱስ ስለ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወቅታዊ ሁኔታ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አሰልጣኙ በሰጡት ቃል “ አሁንም ሁሉም ነገር ክፍት ነው በሩ አልተዘጋም “ ሲሉ መመለስ እንደሚችል ተናግረዋል። “ ሮናልዶ ስለወደፊት ቆይታው በራሱ ይወስናል “ ያሉት አሰልጣኙ “…
1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.