ከ2 ሚሊዮን 4 መቶ ሺ ብር በላይ የሚያወጡ ቴሌቪዥኖችን በመስረቅ እና በመግዛት የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በአቃቤ ህግ ክስ ተመሰረተባቸው
ተጠርጣሪዎቹ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 9 ሰዓት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 5 CC CC ከሚባል የቻይና ድርጅት መጋዘን ውስጥ የቴሌቪዥን ስርቆቱን መፈጸማቸው ተገልጿል።
ተጠርጣሪዎች መገርሳ መሳ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ ፍሩይ ሃጎስ እና ልሳነወርቅ ወሉ ይባላሉ። የቻይና CC CC ድርጅት ሾፌር መገርሳ መሳ እና የመጋዘኑ ጥበቃ ተመስገን ደሳለኝ በስራ ላይ እያሉ የተጣለባቸውን እምነት ወደ ጎን በመተው በድርጅቱ ንብረት ላይ ወንጀል ለመፈጸም ተነጋግረው ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ።
ግለሰቦቹ ያሴሩት ሃሳብ ፍሬ አፍርቶ ከመጋዘን ውስጥ ታሽገው ተቀምጠው የነበሩትን የዋጋ ግምታቸው 2 ሚሊዮን 430 ሺ ብር የሚገመቱ 9 ባለ 54 ኢንች ቴሌቪዥኖችን በራሱ በድርጅቱ አምቡላንስ አውጥተው ከጫኑ በኋላ ቀድመው ላዘጋጇቸው ፍሩይ ሀጎስ እና ልሳነወርቅ ወሉ ለተባሉ ግለሰቦች ሸጠው ወደ ስራ ቦታቸው መመለሳቸውን የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።
የድርጅቱ ጥበቃና ሾፌር እቃዎቹን ሸጠው ወደ ስራ ቦታቸው በመመለስ ስራቸውን እየሰሩ ባለበት ሁኔታ ላይ በመጠራጠር የንብረት ቆጠራ ሲደረግ የተቀመጡ ቴሌቪዥኖች መጋዘን ውስጥ እንደሌሉ ሲረጋገጥ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ፖሊስ ምርመራ እና ፍለጋ መጀመሩ ተገልጿል።
ፖሊስ ምርመራውን በድርጅቱ ጥበቃ ላይ በመጀመር የአምቡላንስ ሾፌሩን ጨምሮ በቁጥጥር ስር በማዋል ሁለቱን ገዢዎች በምሪት ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ሊያውል መቻሉን የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስረድቷል።
በማስረጃ የተደገፈ መዝገብ በማደራጀት ለአቃቤ ህግ መላኩን የጠቆመው ፖሊስ መምሪያው ፈጣን ችሎት ቀርቦ ክስ መመስረቱን አመላክቷል።
ድርጅቶች መሰል የወንጀል ድርጊት እንዳይፈጸምባቸው ከሰራተኛ ቅጥር ጀምሮ የተቀጣሪዎችን እና የሚያቀርቧቸውን ዋሶች ትክክለኛ ማንነታቸውን የሚገልጽ ሰነድ መያዛቸውን በማረጋገጥ ከተቀጠሩም በኋላ የቁጥጥርና ክትትል ስራውን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።
#ዳጉ_ጆርናል

1 day ago