የትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ አደረገ
የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ለወሰዱና በ2019 ዓ.ም በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ለመሰልጠን ለሚወዳደሩ አመልካቾች የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።
ሚኒስቴሩ ለክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች በላከው ይፋዊ ደብዳቤ፣ ውሳኔው የክልሎችን ነባራዊ ሁኔታና የፈተና ውጤት ያገናዘበ መሆኑን ገልጿል።
በዚህም መሰረት ለዲፕሎማ (12+2) ፕሮግራም፦
ለተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ፡ ለወንዶች 215 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች 205 እና ከዚያ በላይ፤
ለታዳጊ ክልሎች፣ አርብቶ አደሮችና አካል ጉዳተኞች፡ 185 እና ከዚያ በላይ፤
ለዓይነ ስውራን (ማህበራዊ ሳይንስ)፡ 150 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተወስኗል።
ለሰርተፊኬት (12+1) ፕሮግራም፦
ለተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ፡ ለወንዶች 210 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች 195 እና ከዚያ በላይ፤
ለታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች፡ 180 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ መቁረጫ ነጥብ የሚያገለግለው ለ2019 ዓ.ም የዕጩ መምህራን ውድድር ብቻ ሲሆን፣ የቀሩት መስፈርቶች በመመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይደረጋሉ ተብሏል።
Seledadotio

1 day ago