(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሱዳን ጦር ሀይል 4ተኛ እግረኛ ክፍለ ጦር ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ሚንዛ እና ባሽካርካድ በተሰኙ አካባቢዎች በፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ (RSF) እና አጋሮቹ የተሰነዘረበትን ጥቃት በብቃት መመከቱን አስታውቋል። ሱዳን ትሪቢዩን እንደዘገበው፣ የሱዳን ጦር ባካሄደው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ የተፋላሚዎቹን በርካታ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች እና ቁሳቁሶች ማውደሙን እንዲሁም ታጣቂዎቹን አባርሮ ወደኋላ እንዲያፈገፍጉ ማድረጉን ገልጿል። ይህ ከባድ ውጊያ የተካሄደው ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ የብሉ ናይል ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ዳማዚን ላይ የድሮን ጥቃት ከፈፀመ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነው። የሱዳን ባለስልጣናት የድሮን ጥቃቱ መፈፀሙን ቢያረጋግጡም፣ ስለደረሰው የጉዳት መጠን እስካሁን ያሉት ነገር የለም።
በሌላ በኩል፣ ይህ የሱዳን ጦር መግለጫ በወጣ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ አጋር የሆነው የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ - ሰሜን (SPLM-N) የራሱን የድል ዜና ይዞ ወጥቷል። አማፂ ቡድኑ ከኢትዮጵያ ድንበር እና ከዳማዚን ከተማ አቅራቢያ የሚገኘውን ስትራቴጂካዊውን "አል ካዳሎ" ዞን መቆጣጠሩን አስታውቋል። ንቅናቄው በዚህ ዞን ውስጥ የሚገኙ 8 ቦታዎችን መያዙን፣ 20 የውጊያ ተሽከርካሪዎችን መማረኩን እና በርካታ የሱዳን ጦር ወታደሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል። ይህንን የድል የይገባኛል ጥያቄ የሚያሳይ የቪዲዮ መረጃም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መሰራጨቱን ዘገባው አመላክቷል።
የአማፂያኑ ቀጣይ ወታደራዊ ግብ የብሉ ናይል ዋና ከተማ ወደሆነችው ዳማዚን ከተማ ሰብሮ መግባት መሆኑ ተነግሯል። የሁለቱ ኃይሎች ተቃራኒ መግለጫዎች እና የውጊያው አድማስ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ይበልጥ መቅረብ፣ በቀጠናው ያለውን የፀጥታ ስጋት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሶታል።

1 day ago