የመደመር አንቀጽ
አንድ ሰው ተሹሞ በመገናኛ ዜናው ሲሰማ በብዙኃኑ ዘንድ የሚነሱት የመጀመሪያዎቹ ጥያቄዎች ብሔሩ ምንድነው፤ ሃይማኖቱስ፤ ሠፈሩስ እያለ ማንነቱን የሚያጣሩ ናቸው።
በአብዛኛው ከነአካቴው የማይነሡ፤ ከተነሡም ከማንነት ማጣራት ቀጥሎ የሚዘሩ ከዚህ በፊት ምን ሠርቷል፤ ለቦታው ብቁ ነው ወይ? ምን ልምድ አለው የሚሉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡
እነዚህ የማንነት ጥያቄዎች ቀድመው የሚመጡበት ምክንያት፤ ልሂቃኑ በሰውዬው ላይ የሚኖራቸው እምነት የሚመነጨው ከማንነቱ በመሆኑ ነው።
የሐሳብ ገበያ ማለት አንድ ሐሳብ ከአቅራቢው ማንነት፣ ሥልጣን ወይም የኋላ ዳራ ተለይቶ በመቅረብ፣ ልክ እንደ ሸቀጦች ሁሉ፣ በሐሳብ ልውውጥ የተሻለ ተቀባይነት የሚያገኝበት መንገድ ነው።
መነሻው የነጻ ገበያ ኢኮኖሚ ሐሳብ ነው። በነጻ ገበያ ኢኮኖሚ ውስጥ የተለያዩና ብዙ ሸቀጦች ይቀርባሉ፡፡ ሰዎች አሳቢዎችና በምክንያት የሚንቀሳቀሱ ስለሆኑ፣ አመዛዝነውና መርጠው የተሻለውን ሐሳብ ይመርጣሉ።
የመደመር መንግስት
ገጽ 380
#ኢትዮጵያ #መደመር #ebc #ethiopia #መንግስ #ኢትዮጵያ #መደመር #ebc #ethiopia #መንግስት Ethiopian Broadcasting Corporation

1 day ago