የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የማቲዎስ ወንዱ-የኢትዮጵያ ካንሰር ማህበር (የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን) መስራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ወንዱ በቀለ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም ረፋድ ከዚህ ዓለም ተለይተዋል።
አቶ ወንዱ ወጣቱን ልጃቸውን ማቲዎስን በካንሰር በሽታ ካጡ በኋላ፣ ያጋጠማቸውን የግል ሃዘን ወደ ህይወት ዘመን አገር አቀፍ ተልዕኮ በመቀየር በኢትዮጵያ የካንሰር ህሙማን እንክብካቤ፣ ግንዛቤ ማስጨበጫ እና የህዝብ ጤና ፖሊሲ ተሟጋችነት ዘርፍ ታላቅ አሻራ ያኖሩ አንጋፋ ሰው ነበሩ።
በፋውንዴሽኑ ስር በመሆን በሺዎች የሚቆጠሩ የካንሰር ህሙማንን (በተለይ ሴቶችን እና ህፃናትን) የህክምና፣ የስነ-ልቦና እና የማህበራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ አድርገዋል።
ህብረተሰቡ ስለ ካንሰር ያለው ግንዛቤ እንዲለወጥ እና በበሽታው ዙሪያ የነበረውን ስጋትና ማህበራዊ ጫና ለመቀነስ ሰፊ አገር አቀፍ ንቅናቄዎችን መርተዋል።
ከካንሰር እንክብካቤ ባለፈ በሀገሪቱ የህዝብ ጤና ፖሊሲዎች በተለይም የትንባኦ ቁጥጥር ስራዎች እና የህግ ማዕቀፎች እንዲጠናከሩ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል።
#ዳጉ_ጆርናል

3 days ago