ኩኩ ሰብስቤ እና ኤልያስ መልካ — «እንባዬ» የሙዚቃ ቪዲዮ ትዝታ
(ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
«ከዘፈኑ ይልቅ ኤልያስን ክሊፑ ላይ ሳየው ነው የኔ ትዝታ» — ተወዳጇ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ።
ድንቁ የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ ካረፈ ዛሬ ሰባት አመታት ተቆጥረዋል ከእልፍ ሙዚቃዎቹ ውስጥ አንዱን መዘን እንገቃችሁ «እንባዬ» የተሰኘው የታወቀ የሙዚቃ ሥራ በመጀመሪያ በክቡር ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ የተዜመ የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ በድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ድምፅ እንደ አዲስ የተሠራ ድንቅ ሥራ ነው። ትንሽ ጊዜ ስጠኝ የተሰኘ አልበም ላይ የተካተተ ነው፡፡ ሙዚቃው በቅንብር፣ በድምፅ ጥራትና በእንቅስቃሴ ስልት ተሻሽሎና ተውቦ በመቅረቡ የብዙዎችን ቀልብ ሊስብና ትልቅ ቦታ ሊይዝ ችሏል።
ይህንን ሙዚቃ እንደ አዲስ አሳምሮ ያቀናበረው ደግሞ ባለብዙ ሙያና ተወዳጁ ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ነበር። ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ስለ ኤልያስ ታስታውሳለች፤ «ገና ሙዚቃውን ሲሰማው ደስ አለው፤ የክራሩን ቅኝት እንዴት አድርጎ እንደጨመረበት አሁንም ቢሆን በዓይነ ሕሊናዬ ይታየኛል፤ እሱ ራሱ ሠርቶ እንደ አዲስ ይደሰት ነበር» በማለት ምስክርነቷን ትሰጣለች።
ሥራውን በበለጠ ለማሳመር የሙዚቃ ቪዲዮ (ክሊፕ) ለመቅረጽ ስታስብ ከኤልያስ ጋር ተወያየች። «ለዚህ ዘፈን ክሊፕ እንስራ፤ አንተ ግራንድ ፒያኖ ላይ ተቀምጠህ ሱፍህን (ቶክሲዶ) አድርገህ በንጋታው ብቅ በል» አለችው። ኤልያስም በደስታ «እሺ እንዴ! ምን ችግር አለው?» ብሎ ተስማማ። ነገር ግን በነገው ዕለት ለቀረጻ ሲመጣ ቱታ አድርጎ ነበር። ኩኩም «እንዴ! እንደዚያ ተቀጣጥረን አልነበረም ወይ?» ስትለው፣ ኤልያስ ፈገግ የሚያደርግ ምላሽ አዘጋጅቶ ነበር— «ባክሽን አሰብኩበትና ደከመኝ፤ ፊቴን አዙሬ ፒያኖው ላይ እቀመጣለሁ እንጂ ሙሉ አልታይም» አላት። ኩኩም «ይሁን፣ ይሁን፤ ዋናው የአንተ መገኘት ነው» ብላ በመስማማት ክሊፑ ተቀረጸ።
ከጊዜያት በኋላ ኤልያስ ካለፈ በኋላ ኩኩ ያንን አጋጣሚ ስታስታውስ፤ «አሁን አሁን ሳስበው ሙሉ ፊቱን አዙሮ ቢሆን ኖሮ ብዬ እቆጫለሁ፤ ይሄዳል ብለን ማን አሰበና!» በማለት በቁጭት ትናገራለች። አክላም «ከዘፈኑ ይልቅ ኤልያስን ክሊፑ ላይ ሳየው ነው ትዝታው የሚቀሰቀሰው፤ ኤልያስ በብዙ ክሊፖች ላይ አይታይም፣ በልቤ ውስጥ ግን ሁልጊዜ ይኖራል» ስትል ጥልቅ ስሜቷን ገልጻለች።
በሕይወት ውስጥ እንዲህ ዓይነት ነገሮች ቁጭት ቢፈጥሩም፣ ትልቅ ማስታወሻና መታሰቢያ ሆነው ያልፋሉ። አንድ ቀን ትዝታ ሆኖ ይጠቅመኛል ብላችሁ በማሰብ ሥራችሁን በተጠንቀቅና በነፍስ ሥሩ። የኤልያስ መልካ ድንቅ የቅንብር ሥራዎች ምንጊዜም እንደ አዲስ እትም ሲታደሱ ይኖራሉ።
ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

2 days ago