በመቐለ ከተማ ለቀናት ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ ተመለሰ
ላለፉት 10 ቀናት በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ መጀመሩን የከተማይቱ አራት ነዋሪዎች ገልጸዋል። አገልግሎቱ ወደ ነበረበት የተመለሰው ዛሬ እሁድ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ተኩል ገደማ መሆኑን ነዋሪዎቹ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ተናግረዋል።
በአብዛኛው የትግራይ ክልል አካባቢዎች በመንግስታዊው ኢትዮ ቴሌኮም ይሰጡ የነበሩት የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎቶች የተቋረጡት ሐሙስ መስከረም 14 ቀን ምሽት ላይ እንደነበር ይታወሳል። ሌላኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ድርጅት የሆነው የሳፋሪኮም ኔትወርክም ቢሆን እስከ አርብ እኩለ ቀን ድረስ ሲሰራ ቆይቶ መቋረጡ ተገልጿል።
የኢትዮ ቴሌኮም እና የሳፋሪኮም አገልግሎት አቅራቢዎች የኢንተርኔት እና የስልክ ኔትወርኮቻቸውን እንዲያቋርጡ ትዕዛዝ የሰጠው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሆኑን የዲፕሎማቲክ ምንጭን ጨምሮ ስለጉዳዩ የሚያውቁ አራት ግለሰቦችን ጠቅሶ ሮይተርስ በወቅቱ ዘግቦ ነበር።
ዛሬ እሁድ ማለዳ አገልግሎቱ ወደ ነበረበት መመለሱን ያረጋገጡት የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች፤ በአሁኑ ወቅት በቀጥታ ስልክ መደወል እንደቻሉ እና የኢንተርኔት አገልግሎትንም በአግባቡ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ገልጸዋል።

2 days ago