Logo
AHADU RADIO FM 94.3
የሀገር ውስጥ ነጋዴዎች በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያግዝ ስምምነት ተፈረመ

የሀገር ውስጥ ነጋዴዎች በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና የንግድ መረጃዎችን በቀላሉ በማግኘት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያግዝ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) እና የአፍሪካ ኤሌክትሮኒክ ንግድ ግሩፕ ናቸው።

ይህ ስትራቴጂካዊ ስምምነት የአዲስ ቻምበር አባል ኩባንያዎች እና መላው የንግድ ማኅበረሰብ አባላት በዲጂታል ንግድ እና በገበያ ትስስር አቅማቸውን እንዲገነቡ ያስችላል ተብሏል።

በተጨማሪም መካከለኛ እና አነስተኛ የንግድ ተቋማትን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የመረጃ፣ የቴክኖሎጂ እና የአቅም ግንባታ ድጋፎች እንደሚደረጉ ተመላክቷል።

የስምምነት ሰነዱን የአዲስ ቻምበር ዋና ፀሐፊ አቶ ዘካርያስ አሰፋ እና የአፍሪካ ኢ-ትሬድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚስ ትሬዠር ማፋንጋ ተፈራርመውታል።

የአፍሪካ ኤሌክትሮኒክ ንግድ ግሩፕ በአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የሚንቀሳቀስ ፓን አፍሪካዊ ተቋም ሲሆን የአህጉሪቱን የእርስ በእርስ ንግድ ለማሳደግ የምስራቅ አፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፍቶ እየሰራ ይገኛል።

ተቋሙ የአፍሪካ ሕብረት የ2063 አጀንዳን እውን ለማድረግ በአህጉሪቱ 5 ሀገራት ቅርንጫፎች ከፍቶ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሆነ ታውቋል።

አዲስ ቻምበር በበኩሉ ላለፉት 80 ዓመታት የንግዱ ማኅበረሰብ እንደራሴ ሆኖ የንግድ ልማት ድጋፍ ሲሰጥና ለኢንቨስትመንት ስራ አመቺ ሁኔታዎችን ሲፈጥር የቆየ ተቋም ነው።

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.