" ታጣቂዎች ለሊት መጥተው በር ሰብረው ነው ይዘዋቸው ይሄዱት " - የቤተሰብ ምንጭ
ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደና ሌሎች አብረዋቸው ታስረው የነበሩ አመራሮች ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን የቅርብ ቤተሰብ ምንጭ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋገጡ።
ላለፉት ዘጠኝ ቀናት በመቐለ በእስር ላይ የነበሩት የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ እና ሌሎች ከፍተኛ የትግራይ ኃይል አመራሮች ትላንት ሌሊት ነው ከመቐለ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸው የተገልጸው።
ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ጋር ከተወሰዱት መካከል የትግራይ ኃይሎች የመረጃና ደህንነት ኃላፊ የነበሩት ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሳኤ እና የትግራይ ኃይሎች የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ የነበሩት ኢሳያስ ታደሰ ይገኙበታል።
እኚሁ የቤተሰብ ምንጭ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፣ የሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ጠባቂዎች መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም. በተቀየሩ ማግስት ቤተሰቦቻቸው ወደ ቤቱ መግባትም ሆነ ከቤቱ መውጣት እንዳይችሉ ተደርጎ ለ18 ሰዓታት ያህል በቤታቸው ተዘግተው እንደቆዩ ተናግረዋል።
ከዚያም በማግስቱ ከቤታቸው አስወጥተው ወዳልታወቀ ቦታ እንደወሰዷቸው ገልጸዋል።
በኋላም ከሌሎች የቀድሞ የትግልና የስራ አጋሮቻቸው ጋር በመቐለ ላጪ ክፍለ ከተማ በሚገኘው " HZ ሆቴል " ታስረው እንደነበር አመልክተዋል።
የህወሓት አመራሮች መቐለን ለቀው ለመውጣት በተዘጋጁበት ወቅት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደንና ሌሎች ታሳሪዎችን ከታሰሩበት ቦታ ለማውጣት ሙከራ ተደርጎ ነበር። ታሳሪዎቹ ግን " አንድሄድም / አንወጣም ከዚህ " በማለት ተከላክለው እንደነበር የቤተሰብ ምንጩ ገልጸዋል።
እስከ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም. ሌሊት 9፡00 ሰዓት ድረስ በዚህ ሁኔታ ከቆዩ በኋላ ታጣቂዎች ታሳሪዎቹ የነበሩበትን ክፍል በመስበር ገብተው በኃይል ከሆቴሉ አውጥተዋቸዋል። ታጣቂዎቹ ታሳሪዎቹን ከሆቴሉ አውጥተው ወደ አዲግራት አቅጣጫ እንደወሰዷቸው ተገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #tigray #mekelle የሀገር መከላከያ ሰራዊት የመቐለ መግቢያዎችን ፣ ኤርፖርቱን ጨምሮ በርካታ የትግራይ ክልል አካባቢዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰማ። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ሰላም ኃይል ጋር በመቀናጀት የመቐለ መግቢያ አካባቢን ፤ ኤርፖርቱን ጨምሮ የክልሉን ሰፊ አካባቢዎች በቁጥጥራቸው ስር ማዋላቸውን ጉዳዩን የሚከታተሉ የቅርብ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። " ወታደራዊ…

3 days ago