Logo
FastMereja
በአዲስ አበባ 10 ሺህ ስኒ ቡና በማጠጣት በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ለመመዝገብ ያለመ መርሃ ግብር ተካሄደ
#fastmereja I በዘንድሮው የኢሬቻ ዋዜማ የኢትዮጵያን የቡና ባህል፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ትስስር የሚያጎላ ታላቅ የቡና መጠጣት እና በአፍሪካ ድንቃድንቅ ሪኮርድ የማስመዝገብ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በግዮን ሆቴል ተካሂዷል።

በኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይንመንትና ኤቨንት ኦርጋናይዘር አዘጋጅነት በተዘጋጀው በዚህ መርሃ ግብር በርካታ ሴቶች ቡናውን በማፍላትና በማስተናገድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን፣ 10 ሺህ ቡና ሲኒ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በአንድ ቦታ ተሰባስበው ቡና እንዲጠጡ ተደርጓል።

ዝግጅቱ የኢትዮጵያን የቡና ባህል በዓለም አቀፍ እና በአፍሪካ ደረጃ በድንቃድንቅ መዝገብ (Guinness World Records) ላይ ለማስመዝገብ ያለመ ታላቅ ጥረት አካል መሆኑም ተጠቅሷል።

በዝግጅቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ታድሟል።

4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.