ኢትዮጵያ በጎረቤት ሶማሊያ ካሰፈራቸው ወታደሮች መካከል ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ለማስወጣት ማቀዱ ተዘገበ።
ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ምንጮችን ጠቅሶ 'ብሉምበርግ' የዜና አውታር እንደዘገበው፤ የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ የሚያደርገው መውጣት በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። የውሳኔው ዋነኛ ምክንያትም፣ የፌዴራል መንግስቱ ከታጣቂ ቡድኖች ጋር እያደረገ ያለው ውጊያ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱን ተከትሎ፣ ተጨማሪ ወታደራዊ ኃይልን ወደ ሀገር ውስጥ ማዛወር በማስፈለጉ ነው ተብሏል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በሶማሊያ የተለያዩ ግዛቶች ማለትም በጌዶ፣ ባይ፣ ባኮል እና በተወሰኑ የሂራን አካባቢዎች ሰፍረው ይገኛሉ። በነዚህ አካባቢዎች ከሚገኙት የኢትዮጵያ ኃይሎች መካከል የተወሰኑት በአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስር የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ፣ ሌሎቹ ደግሞ በአዲስ አበባ እና በሞቃዲሾ መካከል በተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት የተሰማሩ መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።
Seledadotio

4 days ago