የድሬዳዋ ምክር ቤት አቶ አብዱላሒ ሐሰንን የአስተዳደሩ ከንቲባ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒን አፈ-ጉባኤ አድርጎ መረጠ
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው መስራች ጉባኤ አቶ አብዱላሒ ሐሰንን የአስተዳደሩ ከንቲባ፣ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒን ደግሞ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አድርጎ መርጧል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ አቶ ሀርቢ ቡህ ወርሰሞን ምክትል አፈ-ጉባኤ አድርጎ ሾሟል።
በጉባኤው ላይ የተሾሙት አመራሮችና የምክር ቤቱ አባላት ሕዝብና መንግሥት የሰጣቸውን ኃላፊነት በታማኝነትና በፍትሐዊነት ለመወጣት በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
አዲሱ ከንቲባ አቶ አብዱላሒ ሐሰን በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር በከተማውና በገጠር የተጀመሩ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች በፍጥነትና በጥራት እንዲጠናቀቁ በትኩረት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

4 days ago