Logo
YeneTube
ከሰባት ዓመታት በላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን በርዕሰ መስተዳድርነት ሲመሩ የቆዩት አቶ አሻድሊ ሀሰን፤ በስልጣናቸው እንዲቀጥሉ ተመረጡ።

አሻድሊ በርዕሰ መስተዳድርነታቸው እንዲቀጥሉ የተመረጡት፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ዛሬ አርብ ባካሄደው መስራች ጉባኤ ነው።

አቶ አሻድሊ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚገኝበትን ክልል መምራት የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን በመጡ በጥቂት ወራት ልዩነት ውስጥ ነው።

የቀድሞው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አህመድ ናስር ድንገት በሞት ሲለዩ፤ የክልሉ ስድስተኛ መሪ ሆነው በሰኔ 2011 ዓ.ም. የተኳቸው አቶ አሻድሊ ናቸው።

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር መጨረሻ በተካሄደው ምርጫ መሰረት የተመሰረተው፣ 205 አባላት ያሉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት፤ በዛሬው ጉባኤው ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በተጨማሪ የምክር ቤቱን አፈ-ጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤዎች መርጧል።

በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያለው እና መንግስት የመሰረተው የብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር፤ በአቶ ዚያድ አብዱላሂ መተካታቸው ተገልጿል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube FikerAssefa
4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.