(ዘ-ሐበሻ ዜና) አገራችን በበርካታ የፖለቲካ ትኩሳቶች እና የውስጥ አለመረጋጋት ተጠምዳ ባለችበት በዚህ የፈተና ዘመን ከተፈጥሮ በኩል ሌላ የህልውና አደጋ ከደጃፋችን እያንዣበበ መሆኑን የዘርፉ ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ። የውሃ ሃብት እና የአየር ንብረት ባለሙያው ዶ/ር ጥሩሰው አሰፋ ይፋ ባደረጉት አስደንጋጭ መረጃ፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታው የማታውቀው እጅግ የከፋ የድርቅ አደጋ ሊገጥማት እንደሚችል አመላክተዋል።
እንደ ዶ/ር ጥሩሰው ትንታኔ በአሁኑ ወቅት ያለው የአየር ንብረት ሙቀት መጠን ከ2.5 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ በማለፉ፣ ክስተቱ "ሱፐር ኤልኒኖ" ወደሚባል አደገኛ ደረጃ ተሸጋግሯል። ይህ የአየር ፀባይ መዛባት፣ በ1975ቱ (እ.ኤ.አ 1982/83) እና በ2008ቱ (እ.ኤ.አ 2015/16) ኢትዮጵያን ከመታው እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለረሃብ ካጋለጠው አስከፊ ድርቅ የከፋ መሆኑን ባለሙያው አብራርተዋል። አልፎ ተርፎም ይህ ሁኔታ ይበልጥ እየተጠናከረ መጥቶ ወደ "ሀይፐር ኤልኒኖ" ሊያድግ እንደሚችልም ስጋታቸውን አጋርተዋል።
ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ እና ውስብስብ የሚያደርገው ደግሞ፣ ከተፈጥሮ ቁጣው ጎን ለጎን በአገሪቱ ያለው የጸጥታ መደፍረስ እና የነዳጅ አቅርቦት እጥረት፣ አደጋውን በእጅጉ ሊያባብሱት መቻላቸው ነው።
የፖለቲካ ሽኩቻችን እና የርስበርስ መገፋፋቱ የአብዛኛውን ሰው ትኩረት ቢሰርቀውም፣ ተፈጥሮ ግን የራሷን ነጋሪት እያንጓጓች መሆኑን ልብ ልንል ይገባል። ይሁን እንጂ ዶ/ር ጥሩሰው በመልእክታቸው ማጠቃለያ ላይ "አሁንም ለመዘጋጀት ጊዜ አለን!" በማለት፣ መንግስት፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና መላው ህዝብ ከወዲሁ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና የመከላከል ስራ ላይ ርብርብ እንዲያደርጉ አገራዊ ጥሪ አቅርበዋል።

4 days ago