Logo
YeneTube
"ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ ለኤርትራ ተላልፈው ሊሰጡ ነው" — ጃዋር መሐመድ

በመቀሌ በቁም እስር ላይ የሚገኙት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ እና ሌሎች የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ወደ ኤርትራ ድንበር ከተማ አሰናብ ሊተላለፉ መሆኑን ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ ገለጹ። ዝውውሩ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት የሚፈጸም ነው ተብሏል።

በዚህ ዝውውር ውስጥ ከሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ፣ በተጨማሪ አቶ ኢሳይያስ ታደሰ፣ ኮሎኔል ተወልደ እምበብ እና ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ ይካተታሉ።

አቶ ጃዋር አሰራሩ በሕይወታቸው ላይ ከባድ አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት አስቸኳይ የሕይወት ዋስትና እና ከለላ እንዲሰጧቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከወራት በፊት በደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት በኃይል ሥልጣን መያዙን በይፋ ተቃውመው ከተናገሩ በኋላ ከአስተዳደሩ ተገልለው በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

@Yenetube Fikerassefa
6 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.