የኢትዮ-ኬንያ የጋራ ብልፅግና ራዕይ፡ ከታሪካዊ ወዳጅነት እስከ ላሙ የነዳጅ ማጣሪያ
*****************
ከታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ እስከ ስትራቴጂያዊው የላፕሴት (LAPSSET) ኮሪደር የተዘረጋው የኢትዮጵያ እና የኬንያ ጂኦግራፊያዊ ቁርኝት በቀጣናው ታሪክ ውስጥ እጅግ የላቀ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ውህደት ምዕራፍ ላይ ይገኛል።
በተፈጥሮ የየተበረከተ የቅርብ ጉርብትና እና የረጅም ጊዜ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር በቀጣናው አስተማማኝ የሰላም ደሴት እንዲፈጠር ትልቅ መሰረት ጥሏል።
ይህ ወንድማማችነት ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እና ከጆሞ ኬንያታ ዘመን ጀምሮ የተዘራ የዲፕሎማሲ ዘር ነው።
በተለይም ኬንያ በ1963 ነፃነቷን ስትጎናፀፍ ኢትዮጵያ ካደረገችው ድጋፍ አንስቶ በ1964 ከተፈረመው የጋራ የመከላከያ ስምምነት ጋር ተዳምሮ የጸጥታ ስጋቶችን በጋራ ለመመከት የሚያስችል ጠንካራ መሰረት የጣለ ታሪካዊ ግንኙነት ነው።
ይህ ጠንካራ መሰረት በቀጣናው የፖለቲካ ውጣ ውረድ ውስጥ የመንግሥታት ለውጥ ሲደረግ እንኳን ሳይናጋ የፀና የሰላም እና የትብብር ማሳያ ሆኖ ዘልቋል።
በአሁኑ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የሚመራው የሁለቱ መንግሥታት ወዳጅነት ከባህላዊ የዲፕሎማሲ ንግግር አልፎ ወደ ተጨባጭ የልማት ትስስር ተሸጋግሯል።
የትናንትናውን የሞያሌ አቧራማ መንገድ ታሪክ አድርጎ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ የሚያገናኘው ዘመናዊ ድንበር አቋራጭ አስፋልት መጠናቀቁ፣ የኬንያው ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ፈሰስ ያደረገው መዋዕለ ንዋይ እና ኢትዮጵያ ለኬንያ ማቅረብ የጀመረችው የኤሌክትሪክ ኃይል የአፍሪካ ቀንድን በጋራ የማስተሳሰር ትልቅ ማሳያ ነው።
የዚህ ታሪካዊ ትስስር ሌላኛው አህጉራዊ ማሳያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኬንያ የሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ በላሙ ወደብ ተገኝተው ጉብኝት በማድረግ ለነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ማኖራቸው ነው።
ይህ ሁነት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና በዜሮ ድምር ፖለቲካ ሳይሆን በመደመር ዕሳቤ አብሮ ለማደግ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
በግንባታው ሂደት እስከ 16 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ነዋይ ሊፈስስበት የታቀደው እና በናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ የሚገነባው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ በቀን እስከ 700 ሺህ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የማጣራት አቅም ያለው ሲሆን ለ60 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
በሦስት ዓመታት ውስጥ ተጠናቅቆ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ የታቀደው ይህ ማጣሪያ፣ ለኢትዮጵያ እና ለሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አስተማማኝ የነዳጅ አቅርቦት በመፍጠር የሎጂስቲክስ ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።
ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት እና በፍጥነት እያደገች ለምትገኘው ኢትዮጵያ፣ የላሙ ወደብ አጠቃቀም እና ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት አማራጭ የባሕር በር ከማግኘት ባለፈ የቀጣናውን የንግድ ደም ስር የሚያነቃቃ ነው።
ይህ አህጉራዊ ስኬት የመንግሥታት ጥረት ብቻ ሳይሆን የግል ዘርፉም አበርክቶ የሚጠይቅ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንኑ የጋራ ልማት በማስመልከት በአህጉራችን የሚገኙ የኢንዱስትሪ መሪዎች ባለሀብቶች እና ሥራ ፈጣሪዎች በአፍሪካ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንዲሁም አህጉራዊ መፃኢ ዕድላችንን የሚወስኑ ለውጥ አምጪ ፕሮጀክቶችን እንዲገነቡ ታላቅ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
በአጠቃላይ የኢትዮ-ኬንያ ታሪካዊ ወንድማማችነት ከምንጊዜውም በላይ የፀና ሲሆን የሁለቱ ሕዝቦች የኢኮኖሚ ትስስር ወደማይቀለበስበት ምዕራፍ ተሸጋግሯል።
የትልቅ ሕዝብ እና የታላቅ ራዕይ ጉዞ የሆነው ይህ ትስስር የቀጣናውን ብልፅግና እውን ማድረጉ አይቀርም።
በሜሮን ንብረት
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
#ethiopia #ethiokenyarelations #lapsset #dangoterefinery #eastafrica #ebc

6 days ago