Logo
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
በልጃቸው የተገደሉት የቀበሌ አስተዳዳሪ

በምዕራብ ጎንደር ቋራ ወረዳ የበደላ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ማሬ ካሳ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ህይወታቸው ማለፉ ተገለጠ። የአካባቢው አስተዳደር ባወጣው የሃዘን መግለጫ፣ ግለሰቡ ህይወታቸው ያለፈው ከፖለቲካዊ ልዩነት ጋር በተያያዘ በራሳቸው ልጅ በተፈጸመባቸው ጥቃት መሆኑን አስታውቋል።

​አቶ ማሬ ካሳ በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ለረጅም ጊዜ በካቢኔ አባልነትና በልዩ ልዩ የአመራር ሃላፊነቶች ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፣ የቀብር ስነ ስርዓታቸው በበደላ ቀበሌ ተፈጽሟል። ነፍሳቸው በሠላም ይረፍ 🙏

(መረጃው የቋራ ወረዳ አስተዳር ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው)
#ዳጉ_ጆርናል
5 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.