በትራንስፖርት እና ህዝብ በተሰበሰበበት ቲክቶክ ከፍተው የሚያድጮሁ ግለሰቦች የሚቀጣ ሕግ እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ
#fastmereja I በሕዝብ ማጓጓዣ ትራንስፖርቶች፣ በካፌዎች፣ በሠርግና በለቅሶ ሥነ-ሥርዓቶች እንዲሁም ሌሎች በርካታ ሕዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች ላይ ስልካቸውን ከፍተው የቲክቶክ ድምፅ በከፍተኛ ድምፅ የሚያስጮሁ ግለሰቦች ድርጊት ከባድ ምቾት ማጣት ፈጥሮብናል ሲሉ የፋስት መረጃ ተከታታዮች ቅሬታቸውን ገለፁ።
በርካታ ተከታታዮቻችን በላኩልን አስተያየት፤ በታክሲና በሕዝብ አውቶቡስ ውስጥ ለሥራና ለትምህርት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እንዲሁም በለቅሶና በሠርግ መሰል ማኅበራዊ ስብሰባዎች ላይ አላስፈላጊ ድምፅ ከፍ አድርገው የሚከፍቱ ግለሰቦች የሰዎችን ዕረፍትና ሰላም በማደፍረስ ላይ ይገኛሉ። ይህ ድርጊት የማኅበራዊ ድንበር ማለፍና የሌሎችን መብት አለማክበር በመሆኑ ድርጊቱን የሚያስቆም እና ጥፋተኞችን የሚያስቀጣ ግልጽ ሕግና መመሪያ ሊወጣ እንደሚገባ ተከታታዮቻችን በጥብቅ አሳስበዋል።
የሥነ-ልቦናና የማኅበራዊ ጉዳይ ባለሙያዎች በበኩላቸው፤ በሕዝብ ፊት ያለ ፈቃድ አላስፈላጊና ከፍተኛ ድምፅ ያላቸውን ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ማደመጥ የሕዝብን የአእምሮ ዕረፍት ከመንሳቱ በላይ ማኅበራዊ እሴቶችንና መከባበርን የሚያስቀር ድርጊት መሆኑን ይናገራሉ። በመሆኑም በሚከተለው ድርጊት ላይ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀትና ቁጥጥር በማድረግ ማኅበራዊ ሥርዓትን ማስከበር እንዳለባቸው አስተያየት ሰጪዎች አፅንኦት ሰጥተውበታል።
በተጨማሪም በሕዝብ ተሽከርካሪዎችና መሰብሰቢያ ቦታዎች ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ለመጠቀም የሚፈልጉ ግለሰቦች የሌሎችን ሰላምና ዕረፍት ላለመንሳት ኤርፎን ወይም ሄድፎን መጠቀም እንደሚገባቸውና ይህንንም እንደ መልካም ማኅበራዊ ባህል ሊያዳብሩት እንደሚገባ ይመከራል።

6 days ago