Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
በዕርዳታ ሰራተኞች እና ንብረቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በእጅጉ እንዳሳሰባቸው የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ አስታወቁ።
​
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የነዋሪዎች እና የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ኦዞኒያ ኦጂየሎ (ዶ/ር) በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ተለዋዋጭ ሁኔታ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አውጥተዋል።

አስተባባሪው በመግለጫቸው በተለይም በቀደመው ግጭት ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ለተደራራቢ የደህንነት ስጋት መጋለጣቸው እና አዳዲስ መፈናቀሎች መከሰታቸው በሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል ብለዋል።

​የሰብአዊ እርዳታ ማህበረሰብ በተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ መስጠቱን ቢቀጥልም፣ በተለይ በቅርቡ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከተከሰተው ውጥረት መባባስ ጋር ተያይዞ በዕርዳታ ሰራተኞች፣ በንብረቶች፣ በቢሮዎች እንዲሁም በሲቪል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በእጅጉ እንዳሳሰቧቸው ገልጸዋል።

​እንደ መግለጫው ማብራሪያ ​በፈረንጆች 2025 እና 2026 መካከል በተጎዱ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የዕርዳታ ድርጅቶች ከፍተኛ የስራ መስተጓጎል ገጥሟቸዋል።

​በታጣቂ ቡድኖች ቢያንስ 10 የሰብአዊ እርዳታ ተሽከርካሪዎች የተዘረፉ ሲሆን፣ እስካሁን የተመለሱት ሁለት ብቻ ናቸው ተብሏል።

​የዕርዳታ ሰራተኞች ላይ የእገታ፣ የማስገደድ እና ወከባ ጥቃቶች የተፈጸሙ ሲሆን፣ የህዝብ ተቋማት እና መሰረተ ልማቶችም መወረራቸው፣ መውደማቸውና ጉዳት እንደደረሰባቸው ተመላክቷል።

​እነዚህ ድርጊቶች የዕርዳታ ስራዎችን ከማስተጓጎላቸውም በላይ ከፍተኛ የዕርዳታ ፍላጎት ባላቸው ማህበረሰቦች ዘንድ ወሳኝ ድጋፍ እንዳይደርስ እንቅፋት ፈጥረዋል ይላል መግለጫው።

​አስተባባሪው የዕርዳታ ሰራተኞችና ንብረቶች በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህግ መሰረት ከጥቃት የተጠበቁ መሆናቸውንና መቼም ቢሆን ኢላማ መደረግ እንደሌለባቸው አሳስበዋል።

የተዘረፉ የሰብአዊ እርዳታ ተሽከርካሪዎች በሙሉ በአፋጣኝና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመለሱ የጠየቁ ሲሆን፣ ሁሉም ወገኖች አለም አቀፍ ህጎችንና መርሆዎችን እንዲያከብሩ፣ የዕርዳታ ስራዎችን ከማደናቀፍ እንዲቆጠቡ እንዲሁም ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ያለምንም እንቅፋት እርዳታ እንዲደርስ ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ ጥሪ አቅርበዋል።

​በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ የሰብአዊ ድርጅቶች ተሽከርካሪዎቻቸውና ቁሳቁሶቻቸው በግልጽ የሚታዩ መለያዎች እንዲኖራቸው፣ የስነ-ምግባር ደንቦችን በጥብቅ እንዲከተሉ እና ከፍተኛ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ አስፈላጊውን የማሳወቂያ ስርዓት እንዲተገብሩ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia ጃፓን ህወሓት/TPLF ወስዷል ያለችውን ወታደራዊ እርምጃ እንደምታወግዝ ገለጸች። የጃፓን መንግሥት በሰሜናዊ ኢትዮጵያ  እየተባባሰ የመጣውን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ ጥልቅ ስጋቱን ገልጿል። ህዝባዊ ወያኔ ሓነት ትግራይ (TPLF) በክልሉ የሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎችን መቆጣጠርን ጨምሮ የወሰዳቸውን ወታደራዊ እርምጃዎች አውግዟል። ሁሉም አካላት ወታደራዊ ውጥረትን እንዲያረግቡና አለመግባባቶችን በውይይት…
6 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.