TK Industrial Group ከኢንዶኔዢያና ሲንጋፖር ኩባንያዎች ጋር የጋራ ኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረመ
#ethiopia | አዲስ አበባ፦ የኢትዮጵያ፣ ኢንዶኔዢያ እና ሲንጋፖር ኩባንያዎች በኢንዱስትሪና በግብርና ምርቶች ዕሴት ጭማሪ ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የጋራ ኢንቨስትመንት (Joint Venture) ስምምነት ተፈራርመዋል።
የኢትዮጵያው TK Industrial Group ከኢንዶኔዢያው PT. INDO SULTAN JAYA እና ከሲንጋፖሩ OLiviaOlea PTE Ltd ጋር የሶስትዮሽ የጋራ ኢንቨስትመንት ስምምነቱን ተፈራርመዋል።
የTK Industrial Group ባለቤትና የኢትዮጵያ የዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሼክ ቶፊቅ ከድር ተቋማቸውን ወክለው ስምምነቱን ፈርመዋል።
በስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን ሙሐመድ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
አቶ ሀሰን እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ካፒታል ብቻ ሳይሆን ዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር፣ እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራን የሚያጠናክሩ ኢንቨስተሮችን ትፈልጋለች።
የዘርፉ ባለሙያዎች ዕውቀትና ክህሎት እንዲዳብር፣ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን፣ የኤክስፖርት አቅም እንዲያድግ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል እንዲፈጠርና የሀገር ውስጥ ገበያ ፍላጎት እንዲሟላ መንግሥት መሰል ኢንቨስትመንቶችን ለማበረታታት በትኩረት እንደሚሠራም ገልጸዋል።
አቶ ሀሰን አክለውም፣ የተመሳሳይ ኢንቨስትመንቶች መስፋፋት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን አቅምና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።
በስምምነቱ መሠረት የግብርና ምርቶችን ዕሴት መጨመር፣ የግብርና ምርቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማቀናበር፣ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር፣ ለሴቶችና ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የኢንዱስትሪ ትስስርን ማጠናከር፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት፣ ኤክስፖርትን ማሳደግና የኢትዮጵያ አምራቾች ዓለም አቀፍ ገበያን እንዲያገኙ ማስቻል ዋና ትኩረቶች መሆናቸው ተገልጿል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢንዶኔዢያና የፓኪስታን አምባሳደሮች፣ የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ሰናይት መብሬ፣ እንዲሁም ከፍተኛ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
#ኢንቨስትመንት #ኢንዱስትሪ #ግብርና #ንግድ #ኢኮኖሚ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

7 days ago