Logo
EBC

#ትልቅሀገር_ትልቅሕዝብ_ታላቅርዕይ

የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የተወሰዱ የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃዎች አበረታች ውጤት አምጥተዋል - ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)
***************

የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም ላይ በሰጡት ማብራሪያ፣ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ትግበራ የዋጋ ግሽበት ከቁጥጥር ውጪ ይሆናል የሚል ስጋት እንደነበረ አስታውሰው፣ ውጤቱ ግን በእጅጉ የተለየ ሆኖ መገኘቱን አክለዋል።

በለውጡ ማዕቀፍ የተከናወነው ማሻሻያ የዋጋ ግሽበትን በዘላቂነት ማረጋጋት መቻሉን ዶ/ር ፍፁም በማሳያ አብራርተዋል።

እ.አ.አ በ2024 ዓመታዊ አማካይ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 26 በመቶ ገደማ እንደነበር ጠቅሰው፣ ከማሻሻያው ከአንድ ዓመት በኋላ ግን የ12 ወራት አማካይ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ ወደ 16 በመቶ መውረዱን ገልጸዋል።

ይህ ከፍተኛ ቅናሽ ሊመዘገብ የቻለው በአጋጣሚ ሳይሆን በጥንቃቄ በተቀረጹ እና ታሳቢ ስጋቶችን በቁጥጥር ስር ባዋሉ የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃዎች አማካኝነት መሆኑን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ይህ አመርቂ ውጤት ሊመጣ የቻለበት ዋናው ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 14 በመቶ የነበረውን የባንኮች ብድር ዕድገት ጣሪያ ቀስ በቀስ ወደ 18 በመቶ እና 24 በመቶ ከፍ በማድረግ በመጨረሻም ጣሪያውን ሙሉ በሙሉ ማንሳቱ መሆኑን አብራርተዋል።

ሁለተኛው ምክንያት መንግሥት የበጀት ጉድለትን ለመሸፈን እንደ ቀድሞው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገንዘብ በመበደር ፈንታ እንደ ሰነድ ሽያጭ ያሉ አሠራሮችን መተግበሩ ነው ብለዋል።

ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ የግብር ፖሊሲን በማሻሻል የገቢ አሰባሰብ እና አስተዳደር አቅምን ማሳደግ መቻሉ መሆኑን ዶር ፍፁም ገልጸዋል።

የፍላጎትና አቅርቦት ክፍተትን ለማጥበብ በግብርና እና ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፎች የተከናወኑ ሰፋፊ ሥራዎችም ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አክለዋል።

ለአብነትም በግብርናው ዘርፍ የተወሰዱ የመስኖ ማስፋፊያ፣ የእርሻ ሜካናይዜሽን፣ የመሬት አጠቃቀም እና መሰል የማሻሻያ እርምጃዎች ምርት እና ምርታማነትን በእጅጉ ማሳደጋቸውን አንስተዋል።

በተለይም በስንዴ ልማት የተገኘው አመርቂ ውጤት ኢትዮጵያን ከአስመጪነት ራስን ወደ መቻል ያሸጋገራት እንደሆነ፤ የአረንጓዴ ዐሻራ እና የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብሮችም የምግብ ምርት አቅርቦትን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን በአብነት ጠቅሰዋል።

በሃና ምንዳሁን
#ethiopia #economy #economicreform #inflationcontrol #nationalbankofethiopia #ebc

9 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.