Logo
Getu Temesgen
አሜሪካ የምትመካበት የጦር ሰፈር ፈጣሪ አዳነላት
#ethiopia | በእንግሊዝ የሚገኝው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ሊፈጸም የነበረው የሽብር ጥቃት መክሸፉ ተገለፀ።

በእንግሊዝ በሚገኘው ታዋቂው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ሊፈጸም የነበረ ታላቅ የሽብር ጥቃት መከሸፉ ተገልጿል።

የአሜሪካ ስትራቴጂካዊ የቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች እና ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የሚገኙበት RAF Fairford በተባለው የጦር ሰፈር አቅራቢያ ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በጦር ሰፈሩ እና በውስጡ ባሉ ወታደራዊ መሠረተ ልማቶች ላይ "ታላቅ ውድመት" ለማድረስ እቅድ አውጥተው እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበር ተብሏል።

ይህ የጦር ሰፈር አሜሪካ በዓለም አቀፍ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎቿ ወቅት እንደ ዋና መነሻ የምትጠቀምበትና የምትመካበት የጦር ሰፈሯ ነው።

ጥቃቱ ቢሳካ ኖሮ ትልቅ ዓለም አቀፍ ውጥረት ይፈጥር እንደነበር ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ጥብቅ የሆነ የደህንነት ጥበቃ እየተደረገ እንደሚገኝ ቢቢሲ ፅፏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #raffairford #usairforce #ukpolice #counterterrorism #militarybase #defencenews #nationalsecurity

10 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.