Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
#russia

የውጭ አካላት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ ሩስያ አሳሰበች።

ሩሲያ በኢትዮጵያ ትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች እንደገና ስለተባባሰው የጸጥታ ሁኔታ ስጋት እንደገባት ገልጻለች።

በመንግሥት ኃይሎች እና ሕገወጥ ስትል በጠራችው የትግራይ ታጣቂ ቡድኖች መካከል ግጭት እንደገና መከሰቱን የሚገልጹ ሪፖርቶች ደርሷት ጉዳዩን እየተከታተለች መሆኗን አሳውቃለች።

ሩሲያ በግጭቱ የተሳተፉ ወገኖች የተደረሱትን የተኩስ አቁም ስምምነቶች እንዲያከብሩ እና አስቀድመው የተደረሱ የመፍትሔ ስምምነቶችን በጥብቅ እንዲተገብሩ ጥሪ አቅርባለች።

የውጭ አካላት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡም አሳስባለች።

ሩስያ፥ የኢትዮጵያን አንድነት እና የግዛት ሉዓላዊነትን መጠበቅ በሀገሪቱ ያሉ ልዩነቶችን ለመፍታት የሚቻልበት መሰረት እንደሆነ እንደምታምን አሳውቃለች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia #uae " ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ለህዝቧ አንድነት፣ የግዛት አንድነት፣ ጸጥታ፣ ደህንነትና መረጋጋት የማያቋርጥ ድጋፍ እናደርጋለን " - የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች (ዩኤኢ) ህወሓት/TPLF እና ከእሱ ጋር የተባበሩ የታጠቁ ኃይሎች በኢትዮጵያ የፌዴራል ኃይሎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጻ ድርጊቱን አወገዘች። በተጨማሪም፣ ህወሓት በትግራይ የተለያዩ የአውሮፕላን ማረፊያዎችን…
9 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.