Logo
Getu Temesgen
‎ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ለ5 (አምስት) አንጋፋ አርቲስቶች መኖሪያ ቤታቸውን አደሰ
‎
‎♦️ ለተጨማሪ 2 (ሁለት) ግለሰቦችም እንዲሁ ቤታቸው እንዲሰራላቸው ሆኗል
‎
‎#ethiopia | ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ፣ ለመላው ላለፉት በርካታ ዓመታት በተለያዩ የጥበብ ዘርፎች ሀገራቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነት ሲያገለግሉ ለቆዩ 5 አንጋፋ አርቲስቶች አዲስ ያስገነባላቸውን ደረጃቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶች በዛሬው ዕለት በይፋ አስረክቧል።
‎
‎አርቲስቶቹ ድምጻዊት ብርቱካን ዱባለ፣ ከ 3,000 በላይ ዜማና ግጥም የደረሰው የኔው አካሉ፣ የሙዚቃ ባለሙያና አቀናባሪ ኮማንደር ሊቀመኳስ አየለ፣ ደራሲ ግርማይ ገ/ ጻዲቅ እና ተዋናይ እና የሙዚቃ ባለሙያው ጸጋዬ ብርሃኔ ይገኙበታል፡፡
‎
‎የአርቲስቶቹ ቤቶች የተገነባው የኢትዮጲያ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በጎ አድራጎት ማህበር ለዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ነው፡፡
‎
‎አንጋፋዎቹ አርቲስቶች ቀደም ሲል ለሀገር እና ለወገን ካበረከቱት አስተዋጽዖ አንጻር በማይመጥናቸው ያረጁ የጭቃ ቤቶች ይኖሩ የነበረ ሲሆን፣ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ያረጁትን የጨቃ ቤቶች ሙሉ በሙሉ በማፍረስ እና በዘመናዊ የግንባታ ዲዛይን በማስገንባት አስረክቧል፤ ቤቶቹ ለአርቲስቶቹ ምቹና የተረጋጋ ህይወት ለመምራት የሚያስችሉ ሙሉ የቤት ቁሳቁሶች ማለትም አልጋ ከፍራሽ ጋር፣ ሶፋ፣ ቲቪ ፣ ቁምሳጥን እና የኪችን ካቢኔት) እንዲሟላላቸው ተደርጓል።
‎
‎ከዚህ ጎን ለጎን የግጥምና ዜማ ደራሲው የኔው አካሉ ቤት በሚፈርስበት ወቅት ግርግዳ ለሚጋሩት አቶ አብደላ ኡመር እና ወ/ሮ ሳዓዳ ናስር ለተባሉ ጎረቤቶች ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ሀላፊነቱን በመውሰድ የነሱን ሁለት ቤቶች ጎን ለጎን በመገንባት እና ዘመናዊ ሶፋ በመግዛት እንዲጠቀሙበት አስረክቧል፡፡
‎
‎በተለይም ወ/ሮ ሳዳት ባለቤታቸው በሞት የተነጠቁ፣ 4 ልጆችን የሚያሳድጉ እና ልብስ በማጠብ የሚተዳደሩ በመሆኑ ድካማቸውን ለመቀነስ የልብስ ማጠቢያ ማሽንን እና ለሌሎች ጉዳዮች የሚሆን የብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ) ከዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ተበርክቶላቸዋል፡፡
‎
‎ለታዋቂው የግጥምና ዜማ ደራሲ ግሩም ሀይሌ መኖሪያ ቤት እድሳት ተጠናቆ ሳለ ከግንባታ ፍቃድ እና ተያያዥ ህጋዊ ሂደቶች ጋር በገጠመው እክል ሳቢያ ዛሬ መረከብ ባይችልም፣ሂደቱ እንደተጠናቀቀ ቤቱ ወዲያውኑ ለደራሲ ግሩም ሀይሌ የሚረከብ ይሆናል።
‎
‎በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ የኮርፖሬት አፌርስ እና ኮሚኒኬሽን ማኔጀር አቶ አብርሃም ዘሪሁን እንደገለጹት፤ "ፋብሪካችን ከንግድ ስራው ጎን ለጎን ለማህበራዊ ኃላፊነት (CSR) ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል።
‎
‎ፋብሪካው ከተመሰረተበት ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 26 ዓመታት ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ የትምህርት ተቋማትን በመገንባት፣ የጤና ተቋማትን በመገንባት፣ የህክምና መሳሪያዎችን በመለገስ፣ የአረጋዊያን መጠለያ በመገንባት፣ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ፈጥኖ በመድረስ፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍና በሌሎችም የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል" ብለዋል። አክለውም" የሀገር ባለ ውለታ አርቲስቶችን መደገፍና ማከበር የኩባንያው ዋና እሴት ነው " ብለዋል።
‎
‎የኢትዮጲያ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በጎ አድራጎት ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ልዑል ጌታነህ በበኩላቸው “ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ለኪነጥበብ ባለሙያዎች እያበረከተ ያለው በጎ አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህም በኢትዮጲያ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ማህበር ስም ለማመስገን እንወዳለን” ብለዋል፡፡
‎
‎ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ በ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል ላይም በተመሳሳይ ለ5 ታዋቂ አርቲስቶች ቤቶችን አድሶ ክሙሉ የቤት ቁሳቁስ ጋር ያስረከበ ሲሆን፤ አነዚህም እርቲስት ችሮታው ከልካይ፣ አርቲስት ሽመላሽ ለጋስ፣ አርቲስት ጸጋዬ ዘርፉ፣ አርቲስት ብርሃኑ በርታ እና አርቲስት ተስፋ ብርሃን ገ/ጻዲቅ ነበሩ፤
‎
‎በዕለቱ በተካሄደው የቁልፍ ማስረከብ ስነ-ስርዓት ላይ አንጋፋና ወጣት አርቲስቶች፣ የዳሽን ቢራ ከፍተኛ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የብዙሃን መገናኛ ባለሙያዎች በተገኙበት ቤቶቹ ለባለቤቶቻቸው ተረክበዋል።
‎
‎ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ በቀጣይም ከህብረተሰቡ ጎን በመቆም ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ "ጥበብን ማክበር - ታሪክን ማክበር ነው!" በሚለው መርሁ የሀገር ባለ ውለታዎችን መደገፉን እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
‎
‎#dashenbeer ​#ethiopia ​#corporatesocialresponsibility #communitysupport #socialresponsibility #csr #ethiopianartists #cultureandart #givingback

12 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.