የመስቀል ደመራ፡ የኅብረ ብሔራዊነታችን ጥንካሬ እና ተስፋ ተምሳሌት
************************
የመስቀል ደመራ ከሃይማኖታዊ ሥርዓቱ ባለፈ የክረምቱን ጨለማ ገፍፎ የብርሃን ንጋት የሚያበስር፣ ሕዝቦች በአንድነት ተሰባስበው የፍቅር እና የአብሮነት ማሰሪያቸውን የሚያጸኑበት ልዩ ሀገራዊ ሁነት ነው።
ይህ ማኅበራዊ እና መንፈሳዊ ትውፊት ዛሬ በሀገራችን እየተገነባ ላለው የጋራ ብልጽግና እና የሰለጠነ ፖለቲካ ትልቅ ምሳሌ ሆኖ ያገለግላል።
አንድ እንጨት ብቻውን ሲቆም ደመራ አይባልም፤ ብርሃንም ሆነ ሙቀት የመስጠት አቅሙ እጅግ አነስተኛ ነው።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እና የሙያ መስኮች ተበታትነው እና ተነጥለው ሲቆሙ፤ ሀገራዊ ብርሃን እና ዕድገትን ማምጣት አይችሉም።
የመደመር መንግሥት እሳቤም እነዚህን የተበተኑ ሀገራዊ አቅሞች እና ልዩነቶች አዋህዶ፣ እንደ ደመራ አስተሳስሮ ለኢትዮጵያ ታላቅ የሰላም እና የዕድገት ብርሃን መስጠት ነው።
የመስቀል ደመራ በሀገራችን የውበት፣ የፍቅር እና የአንድነት ትልቅ ምልክት ነው። ደመራ በመደመር የሚፈጠር ነው፤ እያንዳንዱ እንጨት እና ችቦ ለብቻው ሲቆም የራሱ ውበት ቢኖረውም፣ ተደምሮ እና ተሳስሮ፣ ደመራ ሆኖ ሲቆም ግን መላውን አካባቢ የሚፈታተነውን ጨለማ የሚገፍፍ ታላቅ የብርሃን ምንጭ ይሆናል።
የደመራው እሳት ዙሪያውን የሚያበራው ሁሉም እንጨቶች በአንድ ላይ ተደምረው ደማቅ ብርሃን ሲፈጥሩ ነው።
ዛሬ ኢትዮጵያ የምትመራበት የመደመር እሳቤም ልክ እንደ ደመራው ሁሉ የሁላችንንም አቅም፣ ዕውቀት፣ ባህል እና ልዩነት ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት የሀገራችንን ብሩህ ተስፋ እየገነባ ይገኛል።
የመደመር ፍልስፍና የትናንት መልካም እሴቶችን ሳይጥሉ የዛሬን ጥንካሬዎች በማስፋት እና የነገን ተስፋ በማንገብ የጋራ ብሩህ ሀገርን የመገንባት ዘይቤ ነው።
የመደመር መንግሥት መርህ በቀደምት አባቶቻችን እና እናቶቻችን ጥበብ ላይ ተመስርቶ፣ የዛሬውን ትውልድ አቅም አስተስስሮ፣ ለነገዋ ኢትዮጵያ ብርሃን መስጠት ነው።
የከተማ ውበት እና የሥራ ዕድል ፈጠራን ጨምሮ በየአካባቢያችን የምናየው ልማት እና ሀገራዊ ለውጥ ሁሉ የዚሁ የተደመረ አቅም ውጤት ነው።
ደመራው ተደምሮ ብርሃን እንደሚሰጥ እና ጨለማን እንደሚገፍፍ ሁሉ፣ የመደመር መንግሥትም ኢትዮጵያውያንን በአንድነት፣ በፍቅር እና በሥራ በማስተሳሰር የሀገራዊ ብልጽግናን ብርሃን እየፈነጠቀ ይገኛል።
ልዩነታችንን ውበታችን፣ ኅብረታችንን ደግሞ ጥንካሬያችን አድርገን በመደመር እሳቤ ሀገራችንን ወደ ከፍታ ማማ እናወጣታለን።
በሃና ምንዳሁን
#ethiopia #meskel #demera #medemer #unity #development #ebc #ebcdotstream

12 days ago