የቻይናው መሪ ሺ ዥንፒንግ በዶናልድ ትራምፕ ደማቅ አቀባበል ቢደረግላቸውም ቤጂንግ የፈለገችውን ማሳካት አልቻለችም
ሁለቱ አገራት የንግድ ጦርነታቸውን ለጊዜው ያስቆመውን የንግድ ስምምነት ቻይና ለአንድ አመት የማራዘም ፍላጓት ቢኖራትም ስምምነታቸው ከኖቬምበር እስከ ጃንዩወሪ ለጥቂት ወራት ብቻ ማራዘም እንደቻሉ ተገልፆል፡፡
ይህም በአሜሪካና ቻይና መካከል በታሪፍ፣ በብርቅዬ ማዕድናት እና በከፍተኛ የአሜሪካ ቺፖች ተደራሽነት ላይ ያሉ አለመግባባቶች ለቀጣይ ድርድር እንዲተላለፉ አድርጓል። ቻይና በተጨማሪም የውስጥ ኢኮኖሚዋን ለማጠናከር ወደ ውጭ ገበያ የምትልከውን ምርት መጠበቅ እንደምትፈልግ ተጠቁሟል።
በታይዋን ጉዳይም ሺ ዥንፒንግ የአሜሪካ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ለቤጂንግ ዋና የስጋት ጉዳይ መሆኑን እንደገና አሳይተዋል። የቻይና መሪ አሜሪካ የታይዋንን ነፃነት እንዳትደግፍ ጥሪ ሲያቀርቡ፣ ትራምፕ በጉዳዩ ላይ የሰጡት የህዝብ ምላሽ ግን እስካሁን አልታወቀም።
ቤዛዊት አራጌ
#ዳጉ_ጆርናል

12 days ago