ኦፕንኤአይ የሰራው ኤአይ ኤጀንት የአውስትራሊያ መንግስት ድረ-ገጽን ጥሶ መግባቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩገለፁ
በኦፕንኤአይ (OpenAI) የበለፀገ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኤጀንት ባለፈው ሰኔ ወር የፈቃድ ወሰኑን አልፎ ወደ አውስትራሊያ መንግስት ድረ-ገጽ በመግባት ይፋዊ እና ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን ማግኘት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጊቱን በኤአይ ኤጀንት የመንግስት ስርዓት የተሰበረበት የመጀመሪያው የሚታወቅ አጋጣሚ ሲሉ ገልፀውታል።
ራሱን ችሎ የሚሰራው የኦፕንኤአይ ፕሮግራም ባለፈው ሰኔ ወር የአውስትራሊያ መንግስት የጤና ድረ-ገጽን ጥሶ የገባው ተቀባይነት የሌለው በሆነ መንገድ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ረቡዕ ዕለት በኒውዮርክ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ይህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኤጀንት የጤና ስታቲስቲክስ አገልግሎቱን ይፋዊ እና ሚስጥራዊ ፋይሎች ማግኘት ችሏል።
ኦፕንኤአይ ስለ ሁኔታው ለአውስትራሊያ መንግስት ጥቆማ የሰጠው እስከ መስከረም ወር ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን፣ ያንንም ያደረገው ክስተቱን የሚያብራራ ኢሜይል ለማንኛውም ሰው ክፍት ወደሆነ አጠቃላይ የኢሜይል አድራሻ በመላክ ነበር። ዛሬ ከኦፕንኤአይ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳም ኦልትማን ጋር በመነጋገር አውስትራሊያ በዚህ ክስተት ላይ ያላትን ከፍተኛ ስጋት ገልጬላቸዋለሁ ብለዋል አልባኔዝ።
አክለውም ኩባንያው የሂደቱን ዝርዝር ለስርዓታችን ለማሳወቅ ይህን ያህል ረጅም ጊዜ በመውሰዱ የተሰማኝን ቅሬታ ገልጫለሁ ብለዋል። ምንም ዓይነት ማሳወቂያ ከመደረጉ በፊት እስከ መስከረም 10 ድረስ ፈጅቷል፤ የተደረገውም ማሳወቂያ ቢሆን ለሕዝብ ክፍት ወደሆነ የኢሜይል ሳጥን የተላከ ኢሜይል ብቻ ነበር።
ከኦፕንኤአይ እና ከተፎካካሪው አንትሮፒክ ኤአይ ሞዴሎች ጋር በተያያዙ ተከታታይ የሳይበር ጥቃቶች ምክንያት፣ በላቀ የኤአይ መሳሪያዎች ኃይል ላይ ያለው ዓለም አቀፋዊ ስጋት እየጨመረ መጥቷል። የኦፕንኤአይ መሳሪያው የተከለከሉ መረጃዎችን ለማግኘት ሲሞክር የጤና ምርምር እያካሄደ እንደነበር አልባኔዝ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም መረጃውን እንዳያገኝ በተከለከለ ጊዜ፣ እገዳውን ያልፍ ዘንድ ሌሎች መንገዶችን ፈልጓል ብለዋል።ኦፕንኤአይ የተሻሉ የአሰራር ደንቦች ሊኖሩት እንደሚገባ የሚያውቅ ይመስለኛል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ መግባት ወደሌለበት ቦታዎች የገባ የምርምር ፕሮጀክት ነው ሲሉ አብራርተዋል።
ሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል

12 days ago