Logo
AHADU RADIO FM 94.3
100 አውቶቡሶች ተመድበው በቀን 3ሺህ 500 ተማሪዎች እየተጓጓዙ እንደሆነ ተገለጸ

መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም.  (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ለተማሪዎች ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ 100 አውቶቡሶችን በመመደብ በቀን 3 ሺህ 500 ተማሪዎችን እያጓጓዘ መሆኑን አስታውቋል።

የድርጅቱ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ደገፉ ገብረመድኅን ለአሐዱ ሬድዮ እንደገለፁት ለተማሪዎች አገልግሎት የተመደቡት እነዚህ አውቶቡሶች ከመደበኛ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የተለዩ ናቸው።

ድርጅቱ ካለፈው ዓመት ሰኔ 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ምዝገባ በማከናወን ከትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ አንስቶ አገልግሎቱን መስጠት መጀመሩን አቶ ደገፉ ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅትም በአገልግሎቱ እየተጠቀሙ ያሉት መካከለኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች ከተገኙ ጀምሮ የተሻለ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች የተገኙ ተማሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

እነዚህ አውቶቡሶች ተማሪዎችን በወንበር ልክ በማስተናገድ በትምህርት ቤት መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ላይ ብቻ አገልግሎት እንደሚሰጡ ተጠቁሟል።

ድርጅቱ አገልግሎቱን ከሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች የሚሰበስበው ክፍያ ለነዳጅ እና ለተሽከርካሪዎች መለዋወጫ የሚውል እንጂ ለትርፍ ለማግኝት የታሰበ አለመሆኑን ምክትል ስራ አስፈፃሚው አብራርተዋል።

ተማሪዎች ለመጓጓዣ አገልግሎቱ የሚከፍሉት ወርሃዊ ክፍያ እንደየሁኔታው ይለያያል የተባለ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱን እያገኙ ያሉት የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

በተመስገን ተጋፋው

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ፌስቡክ ገጽ፡- https://web.facebook.com/a...
ቴሌግራም ገጽ፡- https://t.me/ahaduradi
12 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.