Logo
Tikvah-University
#moe

በወሊሶ የፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን በቀጣይ የሚያሳውቅ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የወሊሶ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነባር እና አዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን እስኪገለፅ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ ሚኒስቴሩ ጠይቋል፡፡

በሌሎች የፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተገኝታችሁ ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፣ ለሚያስፈልጋቹ መረጃ በበምስሉ ላይ በተገለፁት ስልኮች መጠየቅ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
14 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.