Logo
Getu Temesgen
"የአምብር ክትፉወ ከረ"

*ለሴቶች መስቀል "የጎመን ክትፎ"ዕለት
#ethiopia | ብዙ አይነት የጎመን ዝርያዎች ቢሆኖሩም ሁሉም አይነት የጎመን ዝርያዎች ግን ለጎመን ክትፎ ተመራጭ አይደሉም።

ለክትፎ የሚሆን ጎመን ለይቶ በማዘጋጀት ፣የተለያዩ ማጣፈጫዎችን ጨምሮ ቂቤ በማንጠር በባህላዊ የጎመን ክትፎ በመጨመር ሽማግሌዎች መርቀው፣ሴቶችና ልጆች ተሰባስበዉ በአንድነት የተዘጋጀዉን በመመገብና ቡና በመጠጣት የጎመን ክትፎ በአልን በደስታ ያከብሩታል።

ክትፎ ከጉራጌ ማህበረሰብ ጋር ያለው ግንኙነት በጣም ጥልቅ ነው።

ይህ ምግብ በእኛ በጉራጌዎች ባህል ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ሲሆን ከምግብነት ባለፈም የማህበራዊና የባህል ትርጉም አለው።

ክትፎ የጉራጌን ህዝብ የባህል ማንነት ከሚያሳዩ ዋና ዋና ነገሮች አንዱ ሲሆን፣ምግቡን የማዘጋጀት እና የመመገብ ባህሉም ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረና የጉራጌን የማህበረሰብ አኗኗርና ወግን የሚያሳይ ነው።

የጎመን ክትፎ በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ለወዳጅ ዘመድና ለእንግዶች የሚቀርብ ተወዳጅ ምግብ ነው።

አንድ ላይ ተሰብስቦ ክትፎ መብላት የቤተሰብንና የጓደኝነት ትስስር ያጠናክራል።

በተለይ እንደ መስቀል እና ሌሎች ክብረ በዓላት ሲከበሩ ክትፎ የደመቀው የበዓሉ አካል ሆኖ ያገለግላል።

ክትፎ ከዕለት ተዕለት ምግብነት ይልቅ ለልዩ አጋጣሚዎች የሚዘጋጅ ነው።

ለአብነት እንደ ሰርግ፣ ሀዘን፣ ቤተሰብ ጉብኝት፣ እንዲሁም የሀይማኖት በዓላት ላይ ክትፎ መቅረብ የተለመደ ነው።

ይህም ክትፎ ምን ያህል እንደሚከበርና ልዩ ቦታ እንደሚሰጠው ያሳያል።

ክትፎ አብዛኛውን ጊዜ ከሌሎች የአካባቢው ባህላዊ ምግቦች ጋር አብሮ ይቀርባል።

ከእነዚህም መካከል ጎመን (ጎመን ክትፎ) እና አይብ ጎልተው የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ ከጤፍ እንጀራ ይልቅ ቆጮ ተብሎ ከእንሰት የሚዘጋጀው ዳቦ አብሮ ይቀርባል።

ይህ ልዩ አዘገጃጀት የጉራጌን የምግብ አሰራር ዘይቤ ልዩና ውብ ያደርገዋል።

ክትፎ በዛሬው ጊዜ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በውጪ ሀገርም ተወዳጅነት ያገኘ ምግብ ቢሆንም፣ አመጣጡና ባህላዊ አሰራሩ እንደዚሁም ጣዕሙ ግን ከጉራጌ ስም ጋር አብሮ የሚጠራ እንደሆነ ይታወቃል።

🖋Gurage Zone Government communication affairs

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #guragemeske #zone #government #communication

14 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.