Logo
AHADU RADIO FM 94.3
የእናቶች ሞት ከፍተኛ የሆነባቸውን ክልሎች በመለየት በትኩረት እንደሚሰራ ጤና ሚኒስቴር  አስታወቀ

መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም.  (አሐዱ ሬዲዮ) ሚኒስቴሩ አንድ እናት አንድ ህይወት አንድ የጋራ ኃላፊነት በሚል መሪ ቃል ከወሊድ በኃላ የሚከሰት የደም መፍሰስ ላይ ያተኮረ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በመድረኩም 100ሺ የነበረውን  የእናቶች ሞት  141 መቀነስ የተቻለ ሲሆን  በሚቀጥሉት  4 ዓመታት  70 ለማድረግ  እየተሰራ መሆኑንም ተገልጻል፡፡

በ 2030 የእናቶችን ሞት ለመቀነስ  የተያዘው እቅድ እንዲሳካ የጤና ባለሙያዎች እና የበላይ አመራሮች በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው በመድረኩ የገለጹት የጤና  ሚኒስትር ዴታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ ናቸው፡፡

የእናቶች ሞት ከፍተኛ የሆነባቸውን ክልሎች በመለየት በትኩረት እንደሚሰራ አንስተው በኢትዮጵያ የእናቶች ሞት አሁንም አሳሳቢ የማህበረሰብ  የጤና ስጋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከወሊድ በኃላ የሚከሰት የደም መፍሰስ ለእናቶች ሞት ቀዳሚ መንስኤ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅርፍ ባለፉት ዓመታት ከተሰሩ  ስራዎች  በአለም አቀፍ ደረጃ  ጊዜውን ያገናዘበ እና በአዳዲስ ጥናቶች ላይ መሰረት ያደረጉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱን ገልፀዋል።

የጤና ሚኒስቴር ከክልል ጤና ቢሮዎች እና አጋር አካላት ጋር በጋራ በመተባበር የእናቶችና ህጻናት ሞት ለመቀነስና ጤናቸውን ለማሻሻል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በህይወቴ ጌትነት

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ፌስቡክ ገጽ፡- https://web.facebook.com/a...
ቴሌግራም ገጽ፡- https://t.me/ahaduradio
15 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.