Logo
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
በኮንሶ ዞን የካላዛር በሽታ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ

👉 በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ 6 ሰዎች በበሽታዉ እንደሚያዙ ተገልጿል፡፡

ካላዛር ሌሽማኒያ በሚባል ተህዋስያን አማካኝነት የሚከሰተዉ የካላዛር በሽታ በኮንሶ ዞን ስርጭቱ ካለፈዉ በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በያዝነዉ በጀት ዓመት ጭማሪ ማሳየቱን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታውቋል ።

በመምሪያዉ የበሽታ መከላከል ዳይሬክቶሬት የወባ እና ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ እና የህዝብ ግንኙነት ፎካል የሆኑት አቶ ገብረ እየሱስ ገመዳ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት በሽታዉ ህክምና ካላገኘ ለሞት ይዳርጋል ።

ባለፉት ዓመታት የበሽታዉ ስርጭት ዝቅተኛ እንደነበር የሚገልፁት አቶ ገብረ እየሱስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በተደረገ ጥናት የበሽታዉ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን ማወቅ ተችሏል ብለዋል ።

በዋናነት የበሽታዉ አምጪ የሆነችዉ ተህዋስ በበረሃ አከባቢዎች በተለይም እንደ ግራር ባሉ የበረሃ ዛፎች ላይ የመራባት ዕድሏ ሰፊ መሆኑ ተጠቅሷል። አልፎ አልፎ የሚከሰት ትኩሳት ፣በግራ የሆድ ክፍል ላይ የሚፈጠር እብጠት ፣የሰዉነት ክብደት መቀነስ ፣ድካም ፣አቅም ማነስ ፣የምግብ ፍላጎት መጥፋት ፣ተቅማጥ እንዲሁም የነስር ህመም የበሽታዉ ምልክቶች ናቸዉ ።

በሽታዉ ህክምና ካለገኘ ለሞት የሚዳርግ በመሆኑ ምልክቶቹ ሲታዩ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ አስፈላጊ ነዉ ተብሏል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
14 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.