Logo
EBC
ምሥራቅ አፍሪካ ሰላም እንዳይሆን የሚሠሩ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ሊቆም ይገባል፦ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
***********************

አፍራሽ ኃይሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሕዝቦች በሰላም እና በብልጽግና የመኖር መብታቸውን እንዲያከብሩ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንቱ በ81ኛ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ከፍተኛ የክርክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ በቀጣናዊ ትሥሥር፣ መሠረተ ልማት እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ስኬት ማረጋገጧን ገልጸዋል።

በአንፃሩም፣ በምሥራቅ አፍሪካ ሰላም እና አብሮነት እንዳይኖር የሚሠሩ አፍራሽ ኃይሎች የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በመቋቋም ከፍተኛ ትዕግሥት እያሳየች መሆኗን ተናግረዋል።

አክለውም፣ በቀጣናው የጋራ ልማትና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ሊቆም ይገባል ብለዋል።

ሱዳንን በተመለከተም፣ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚቻለው በራሳቸው በሱዳናውያን መሪነት እና ባለቤትነት በሚካሄድ የሰላም ጥረት ብቻ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣናው የሚገኙ ተቋማት ለሰላም የሚያደርጉትን ጥረት መደገፏን እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።
#ethiopia #africa #ebc #unga81 #regionalpeace #globalpeace

13 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.