በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ የህወሓት አመራሮች ጥቃት በመክፈታቸው ማዘናቸውን ገለጹ
#fastmereja I በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በህወሓት (TPLF) አመራሮች የተወሰደውን ውሳኔና የተከፈተውን ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት በመቃወም መግለጫ አውጥተዋል። አምባሳደሩ በአዲሱ መግለጫቸው፣ በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለባቸው የህወሓት አመራሮች ሰፊ ጥቃት ለመሰንዘር የወሰዱት ውሳኔ አሳዛኝ እና የተሳሳተ እርምጃ መሆኑን ጠቅሰው፤ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ባመቻቹት የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ውይይት ከመሳተፍ ይልቅ ወደ ማሸነፍ ወደማይቻል አላስፈላጊ ግጭት መግባት ለህዝቡ ምንም ዓይነት ጥቅም እንደማያመጣ አስገንዝበዋል ሲል በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ዘግቧል።
አምባሳደር ማሲንጋ አክለውም ሌሎች ታጣቂ ቡድኖችም ተመሳሳይ አጥፊ መንገዶችን ከመከተል እንዲቆጠቡ መክረዋል። አሜሪካ ኢትዮጵያን ወደተሳሳተ እና አጥፊ መንገድ የሚገፉ ተጨማሪ አመራሮች ላይ ማዕቀብ የመጣል አማራጮችና መሳሪያዎች ያሏት ቢሆንም፣ አሁንም ቢሆን የከረረውን ችግር ለመፍታት ብቸኛው እና ትክክለኛው መንገድ ምክንያታዊ የፖለቲካ ውይይት ማድረግ እንደሆነ የሚያምኑ መሆኑን አምባሳደሩ ባወጡት ይፋዊ መግለጫ ላይ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

13 days ago