የዛሬዋን ዓለም አስቀድሞ የተነበየው የቻርሊ ቻፕሊን ታሪካዊ ንግግር!
ቻርሊ "ስግብግብነት የሰውን ልጅ ነፍስ መርዞታል!"
"ከብልሃት ይልቅ ርህራሔና ደግነት ያስፈልገናል" ብሎ ነበር።
#ethiopia | ዓለም ከተመለከታቸው ድንቅ የጥበብና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል አንዱ ቻርሊ ቻፕሊን "The Great Dictator" በተሰኘው ታዋቂ ፊልሙ ማጠቃለያ ላይ የተናገረው ንግግር ነው።
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማ የፋሺዝምና የባርነት ስጋት ዓለምን ስጋት ላይ በጣለበት ወቅት የቀረበው ይህ ንግግር ለነፃነት ለሰብአዊነት እና ለፍቅር የቀረበ ጥሪ ነበር።
"አዝናለሁ ነገር ግን እኔ ንጉሠ ነገሥት መሆን አልፈልግም።
ሰዎችን መግዛትም ሆነ ማሸነፍ የእኔ ፍላጎት አይደለም።
ቢቻለኝ ሁሌም ሰዎችን መርዳት እንጂ ማናቸውንም ሰዎች አይሁድ ክርስቲያን ጥቁርም ሆኑ ነጭ ብዬ ማግለል አልፈልግም።
ሁላችንም አንዱ ሌላውን መርዳት እንጂ በጠላትነት ማየት የለብንም።
ዓለም ለሁሉም የምትበቃ ስፋትና ሀብት አላት።
የሰው ልጅ ሕይወት ነፃና ውብ ሊሆን ይችላል ነገር ግን መንገዱ ጠፍቶብናል።
ስግብግብነት የሰውን ልጅ ነፍስ መርዞታል ዓለምን በጠላትነት አጥሮታል ወደ ደምና ወደ መከራም መርቶናል።
የቴክኖሎጂና የእውቀት እድገታችን ከሰዎች ጋር ከማቀራረብ ይልቅ ለይቶናል።
ማሽነሪዎች በዛው ልክ ስግብግብነትን እውቀታችን ደግሞ ጨካኝና ክፉ አድርጎናል።
ከማሽኖች ይልቅ ሰብአዊነት ያስፈልገናል።
ከብልሃት ይልቅ ርህራሔና ደግነት ያስፈልገናል።
እነዚህ በጎ እሴቶች ከሌሉ ሕይወት ጨካኝ ይሆናል ሁሉም ነገር ይጠፋል።
በእንደዚህ አይነት ሰብአዊነት ውስጥ የነፃነት ብርሃን አለ።" ሲል ተናግሮ ነበር።
ይህ ንግግር የቻርሊ ቻፕሊን የመጀመሪያው ድምፅ ያለው የፊልም ንግግሩ ነበር።
ይህ ንግግሩ ዛሬም ድረስ በዓለም ዙሪያ ለሰላም እና ለሰብአዊ መብቶች በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ እንደ መነሻ የሚጠቀስ ታሪካዊ ንግግር ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #thegreatdictator #charliechaplin #humanityfirst #peaceandlove #worldpeace #wisdom

15 days ago