ድምፃዊ ኢሳያስ ታምራት በ8 ወር ውስጥ ሰርቶ ያጠናቀቀውን የመጀመሪያ አልበሙ ሊወጣ ነው።
#fastmereja I ድምፃዊ ኢሳይያስ ታምራት 13 ዜማዎችን ያካተተ «ታድዬ» የተሰኘ የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሙን አጠናቆ በቅርቡ ለአድማጮች ሊያደርስ መሆኑ ተገለጸ።
ይህ አልበም በሽርጉድ ኢቨንት ኤንድ ኢንተርቴይንመንት ፕሮዲዩስ የተደረገ ሲሆን ድርጅቱ የአልበሙን ዝግጅት እና ተያያዥ ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ ዛሬ መስከረም 5፣ 2019 በራማዳ አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
«ታድዬ» የተሰኘው ይህ አዲስ አልበም የበርካታ አንጋፋና ወጣት የዜማ የግጥም እንዲሁም የሙዚቃ ቅንብር ባለሙያዎች ጥረት ያረፈበት ልዩ የጥበብ ሥራ መሆኑ ተገልጻል። አልበሙን ለማዘጋጀት 8 ወራት የፈጀ ሲሆን ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ፕሮዲዩሰር እና መምህር አበጋዝ ክብረወርቅ የሙዚቃዎቹን የማስተሪንግ ሥራ አከናውኗል።
በአልበሙ የዜማ እና የግጥም ፈጠራ ላይ በርካታ ስመ ጥር ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በ«13 ወር ጸጋ» የሙዚቃ ሥራው የሚታወቀው አንጋፋው የሙዚቃ ሰው ታምራት አበበ፣ ገጣሚና ደራሲ በውቀቱ ስዩም፣ እንዲሁም ጥልቅ ስሜት ያላቸውን ግጥሞችና ዜማዎች በመድረስ የሚታወቀው አለማየሁ ደመቀ ይገኙበታል።
በተጨማሪም ለአንጋፋና ወጣት ድምፃውያን ውብ ዜማዎችን ያበረከተው ኢንጂነር ፋንታ ወጨፎ፣ በዜማ በግጥም እና በቅንብር ሚና የተሳተፈው ሁለገብ ከያኒ መኮንን ለማ እንደዚሁም እዬቤል ብርሃኑ እና ሰለሞን ሃይለማርያም በግጥምና በድርሰት ሥራዎቻቸው አሻራቸውን ያሳረፉ ባለሙያዎች ናቸው።
በሙዚቃ ቅንብር ረገድ አቤል ጳውሎስ መኮንን ለማ እና ኤርሚያስ ፍቃዱ የተሳተፉበት ሲሆን የዘመናዊና ባህላዊ የዜማ ቅኝቶችን አዋህዶ የያዘው ይህ ሥራ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ውበት ጠብቆ በከፍተኛ ጥራት የቀረበ መሆኑ ተነግሯል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት እንደተገለጸው ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ አልበሞችን አዘጋጅቶ ለማውጣት ረጅም ዓመታት ሊወስድ የሚችል ቢሆንም የ«ታድዬ» አልበም በተጠናከረ የቡድን ቅንጅትና ጥረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ ችሏል።
አልበሙ የፊታችን አርብ በመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም በሽርጉድ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ የዲጂታል መተግበሪያዎች እና የሚዲያ አማራጮች ሙሉ በሙሉ ለአድማጮች ይለቀቃል።

22 days ago