Logo
Getu Temesgen
በህልሙ ባያቸው ቁጥሮች 8 ሚሊዮን ዶላር አሸናፊ የሆነው ግለሰብ!
#ethiopia | በሕልሙ ያያቸውን ቁጥሮች ላለፉት 5 ዓመታት ሲቆርጥ የነበረው ግለሰብ የሎተሪ አሸናፊ መሆኑ ተገለፀ።

አውስትራሊያ ነዋሪነቱን ያደረገው ይህ ግለሰብ በሕልሙ የተመለከታቸውን ቁጥሮች ባለመተው ላለፉት አምስት ዓመታት በተደጋጋሚ ሲቆርጥ እንደነበረ ተገልጿል።

ግለሰቡ ከ5 ዓመታት በፊት በሕልሙ ባያቸው 6 ልዩ ቁጥሮች ተስፋ ሳይቆርጥ በእያንዳንዱ የሎተሪ ዕጣ ወቅት እነዚሁኑ ቁጥሮች ብቻ በመምረጥ ይገዛ እንደነበር ታውቋል።

በርካቶች የዕድል ቁጥራቸውን በየጊዜው ሲቀይሩ እሱ ግን በሕልሙ ያየውን ምልክት እንደ ተራ ነገር ሳይቆጥር በጽናትና በትዕግስት ተመሳሳይ ቁጥሮችን መቁረጡን ቀጥሎበታል።

በቅርቡ በወጣው ይፋዊ የሎተሪ ዕጣ መውጫ ላይ በሕልሙ ያያቸው ሁሉም 6 ቁጥሮች ሙሉ በሙሉ በመውጣታቸው የ8 ሚሊዮን ዶላር ባለቤት ለመሆን በቅቷል።

ግለሰቡ ስለ ዕድሉ ሲናገር ብዙዎች ሕልምን እንደ ተራ ቅዠት ይቆጥሩታል እኔ ግን ሕልሜን አልናቅኩትም ነበር ሲል ተናግሯል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #lotterywinner #dreamtoreality #australianews #inspirationalstory #luckynumbers

22 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.