የቡድን 7 ሀገራት ተፅዕኖን የቀለበሰው የብሪክስ ስብስብ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሪክስ ከዓለም ጠቅላላ ምርት 40 በመቶውን በመሸፈን በገበያ አቅም ጥንካሬ የቡድን 7 ሀገራትን ስብስብ በመብለጥ ቀዳሚ መሆን ችሏል፡፡
የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ድምፃቸውን የሚያሰሙበት የብሪክስ ስብስብ ከመመስረቱ አስቀድሞ የቡድን 7 (G7) አባል ሀገራት ስብስብ የዓለምን ኢኮኖሚና ፖለቲካዊ አቅጣጫ የሚወስን ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብስብ ነበር፡፡
አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን እና ካናዳን ያቀፈው ስብስቡ ከ28 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዓለም ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት እንደሚሸፍን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) መረጃ ያመላክታል፡፡
የቡድን 7 አባል ሀገራት እንደ አይ ኤም ኤፍ እና የዓለም ባንክ ባሉ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪነት ሚና የነበራቸው ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ የንግድ፣ የታክስና የፋይናንስ ህጎችን በማውጣት ረገድ መሪም ነበሩ፡፡
የቡድን 7 ሀገራት አብዛኞቹ የኔቶ አባላት በመሆናቸው በዓለም አቀፍ ደህንነትና ወታደራዊ ስትራቴጂዎች ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አላቸው።
በተለይ ሦስቱ ሀገራት (አሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ) የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት ሲሆኑ፤ በዓለም ላይ የሚነሱ ግጭቶችን ለማስቆም ወይም ተፅዕኖ ለማሳደር ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ማዕቀቦችን በጋራ ሲጥሉ ቆይተዋል፡፡
ሀገራቱ በብቸኝነት በሚወስኑት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎች፤ መገለል የተሰማቸው ሀገራት በፈረንጆቹ 2006 ብሪክስን በመመሰረት የመጀመሪያ ጉባኤያቸውን በ2009 አካሂደዋል፡፡
የዓለምን 49 ነጥብ 5 በመቶ ህዝብ የሚወክለው ብሪክስ አሁን ላይ የአባላቱን ቁጥር 11 ያደረሰ ሲሆን፤ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ተፅዕኖው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡
የብሪክስ ስብስብ ባለፉት አምስት ዓመታት ከዓለም አቀፍ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (Global GDP) 40 በመቶውን ሲሸፍን፤ ይህ ምርት በገንዘብ ሲሰላ ወደ 88 ትሪሊየን ዶላር ገደማ መሆኑን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት መረጃ ያመለክታል፡፡
በአንጻሩ የቡድን 7 አባል ሀገራት ከዓለም ኢኮኖሚ 28 በመቶውን ሲሸፍኑ በገንዘብ 62 ትሪሊየን ዶላር አካባቢ ይገመታል፡፡
አሁን ላይም የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድና የኢኮኖሚ ትብብርን ማጠናከር በአባል ሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እያሳደጉ ይገኛሉ፡፡
አባል ሀገራቱ እርስ በርሳቸው በሚያደርጉት የንግድ ልውውጥ በራሳቸው የመገበያያ ገንዘብ መጠቀማቸው፤ የአሜሪካ ዶላር በዓለም ገበያ ላይ ያለውን ፍጹም የበላይነት ለመገዳደር አስችሏል፡፡
የዓለም ፖለቲካ በአንድ ወይም በሁለት ኃያላን ሀገራት ፍላጎት ብቻ ከመመራት ይልቅ፤ ታዳጊና በፈጣን ዕድገት ላይ ያሉ ሀገራትም እኩል ተጽዕኖ የሚፈጥሩበት ዓለም አቀፍ ሥርዓት በመገንባት ረገድ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ ጥር 2024 የብሪክስ አባል ከሆነች ጊዜ ጀምሮ በስብስቡ ውስጥ በተለይም በኢኮኖሚ፣በዲፕሎማሲና በአየር ንብረት ልማት ዘርፎች ንቁ ተሳትፎን እያደረገች ትገኛለች፡፡
በሚኪያስ አየለ

23 days ago