ፍትሃዊ የዓለም ሥርዓትን የመገንባቱ የብሪክስ ጉዞ እና ተፅዕኖው!
#ethiopia | የብሪክስ ስብስብ ከአለም አቀፍ የኢኮኖሚ የፖለቲካ እና የማህበራዊ እድገት አንጻር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እና እየጎለበተ መጥቷል።
የብሪክስ ስብስብ ለዘመናት የቆየውንና "አንድ ወገን ብቻ የሚወስንበትን" የዓለም የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሥርዓት በመቀየር፣ ፍትሃዊ ሚዛናዊ እና ብዙ ማዕከላት ያሉት አዲስ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምህዳር መገንባት ችሏል።
በአሁኑ ወቅት ስብስቡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግዙፍ ቁጥራዊ እና ስትራቴጂካዊ ተፅዕኖዎች በመፍጠር ላይ ይገኛል።
የብሪክስ አባል ሀገራት የዓለምን ሕዝብ ከ45 በመቶ በላይ የሚሸፍኑ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ደግሞ ከ30 በመቶ በላይ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛሉ።
ይህ ግዙፍ የገበያ እና የሕዝብ አቅም ስብስቡ በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ የኢንቨስትመንት ፍሰት እና የዋጋ ተመን ላይ ወሳኝ ተፅዕኖ እንዲኖረው አድርጎታል።
ስብስቡ ከአለም ባንክ እና ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ውጭ አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ የሚሆን "አዲስ የልማት ባንክ" በማቋቋም ታዳጊ የፖለቲካ ጫና ሳይደረግባቸው ለልማት ፕሮጀክቶቻቸው ብድር የሚያገኙበትን መንገድ አመቻችቷል።
በተጨማሪም አባል ሀገራቱ በሁለትዮሽ ንግዶቻቸው ወቅት የአሜሪካ ዶላርን ከመጠቀም ይልቅ በሀገር ውስጥ ገንዘቦቻቸው መነጋደድ መጀመራቸው የምንዛሬ ተመን መናጋት በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚያደርሰውን ጫና እንዲቀንስ አድርጓል።
ለዘመናት በምዕራባውያን ሀገራት ቁጥጥር ስር የነበሩት እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የጸጥታው ምክር ቤት ያሉ ተቋማት የዛሬውን የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ እንዲሻሻሉ አድርገዋል።
ሀገራት በተቋማቱ ፍትሃዊ ተወካይነት እንዲኖራቸው የብሪክስ ስብስብ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።
የዓለም ግዙፍ የነዳጅ የግብርና ምርቶች እና የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃዎች አምራች ሀገራትን በአንድ ጃንጥላ ስር ያቀፈው ይህ ስብስብ የምግብ ዋስትናን እያረጋገጠ ይገኛል።
በአባላቱ መካከል የሚያደርገው የንግድና የቴክኖሎጂ ሽግግር የዓለምን የምግብ እና የኃይል አቅርቦት ሰንሰለት በማረጋጋት ረገድ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑ መረጃዎች ጠቁመዋል።
የ2026 የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ በህንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላዲሚር ፑቲን፣ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ጨምሮ በርካታ የዓለም መሪዎች ታድመዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #brics2026 #brics #india #newdelhi #narendramodi

26 days ago