Logo
Getu Temesgen
“የጉዞዎን ልምድ ከመደበኛ ወደ ልዩ ያሻሽሉ!” የኢትዮጵያ አየር መንገድ CIP Lounge & Terminal Service
#ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ አዲሱን CIP (Commercially Important Person) Lounge & Terminal Service በግል ተሞክሮ ለማየት እድሉን አግኝቻለሁ።

ይህ የኤርፖርት ጉዞ ከመግቢያ እስከ አውሮፕላን በር ድረስ በተቀናጀ አገልግሎት፣ በምቾትና በግላዊ ትኩረት የሚያልፍ የጉዞ ልምድ ነው።

እናንት ያገሬ ልጆች፣ ግልጽነት ለዘላለም ይኑር!

CIP Service ምን ያካትታል?

* የግል ቼክ-ኢን እገዛ — ረጅም ሰልፎችን በማስቀረት ፈጣንና የተቀናጀ አገልግሎት።

* የሻንጣ አስተዳደር ድጋፍ — ከሻንጣ ማስተናገድ ጀምሮ በሂደቱ ሁሉ የሚደረግ እገዛ።

* የጉምሩክና ኢሚግሬሽን ድጋፍ — የተቀናጀና ፈጣን የሰነድ ሂደት።

* CIP Lounge — ምቹና ጸጥተኛ ማረፊያ፣ የምግብና መጠጥ አገልግሎት፣ የባህላዊ ቡና ሥነ-ሥርዓት፣ Quiet Room፣ የስብሰባ ክፍል፣ የጸሎት ክፍሎችና የሻወር አገልግሎት።

* የግል የመሳፈሪያ እገዛ — ከላውንጁ እስከ አውሮፕላኑ በር ድረስ በልዩ መኪና የሚደረግ ሽኝት።

ኢትዮጵያዊ ሆስፒታሊቲ በCIP Lounge

በላውንጁ ውስጥ ከአገርኛና ከዓለም አቀፍ ምግቦች በተጨማሪ፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና ሥነ-ሥርዓትና ቆሎ መቅረቡ የጉዞውን ልምድ የበለጠ ልዩ ያደርገዋል።

በዚህ ሁሉ ውስጥ የሚታየው የሰራተኞች ትጋትና ፈገግታ ደግሞ የአገልግሎቱ ዋነኛ ማራኪነት ነው።

ሮዛ ወንደወሰን — Lounge Attendant በትህትናና በትጋት ያደረገችልኝ አገልግሎት ከምቾቱ በላይ የሰው ልጅ እንክብካቤ ምን ያህል የጉዞ ልምድን እንደሚቀይር አሳይቶኛል።

በመጨረሻም በሎሪ እስከ አውሮፕላኑ ድረስ ሸኝተውኝ፣ “መልካም ጉዞ” ብለው በመመኘት ተመልሰዋል።

የCIP Service ዋጋ

መደበኛ ዋጋ፦ $150

የቅናሽ ዋጋ፦ $120
በተጠቀሰው የማስተዋወቂያ ጊዜ ውስጥ

ከኢኮኖሚ እስከ ቢዝነስ ክላስ ድረስ የትኬት ዓይነትዎ ሳይወሰን፣ አገልግሎቱን ለመጠቀም ከበረራዎ በፊት በቂ ጊዜ ማሳወቅ ያስፈልጋል።

በአጠቃላይ፣ CIP Lounge & Terminal Service ለእኔ የተለየ የኤርፖርት ተሞክሮ ነበር። ከረጅም ሰልፍና ከተለመደው የጉዞ ግርግር ርቆ፣ ጊዜን በመቆጠብ፣ በምቾት በመቀመጥና በግላዊ እንክብካቤ ጉዞን መጀመር የሚያስችል አገልግሎት ነው።

የጉዞዎን ልምድ ከመደበኛ ወደ ልዩ ያሻሽሉ።
Ethiopian Airlines CIP Lounge & Terminal Service

በአጠቃላይ፣ CIP Lounge & Terminal Service ለእኔ የተለየ የኤርፖርት ተሞክሮ ነበር። ከተለመደው የጉዞ ሂደት ለየት ያለ ፣ ጊዜን በመቆጠብ፣ በምቾት እና በግላዊ እንክብካቤ ጉዞን መጀመር የሚያስችል ቀልጣፋ አገልግሎት ነው።

ለበለጠ መረጃ

https://www.ethiopianairli...

በአቅራቢያ የሚገኘው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት ቢሮ ጎራ ይበሉ

ወይንም

6787 - ይደውሉ

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopianairlines #cipservice #ciplounge #flyethiopian #premiumtravel #travelexperience #ethiopia #ethiopianairlines #cipservice #ciplounge #flyethiopian #premiumtravel #ethiopianhospitality #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

25 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.