Logo
Getu Temesgen
የሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት አጋሮች ለወደፊቱ ትውልድ የሚሻገር ታሪካዊ አሻራ ማኖራቸውን ከንቲባ ጥራቱ በየነ ገለጹ
#ethiopia | የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ለሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ ላደረጉ ባለሀብቶች፣ ተቋማትና ልዩ ልዩ አጋሮች የምስጋናና የእውቅና መርሐ ግብር ያካሄደ ሲሆን፣ በዕለቱ የተገኙት የከተማዋ ከንቲባ ጥራቱ በየነ የአጋሮቹ አስተዋጽኦ ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር አሻራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከንቲባው በንግግራቸው በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ስኬታማ ፍሬ ማፍራት የቻሉት በመንግሥት ጥረት ብቻ ሳይሆን በህዝቡና በአጋሮች ንቁ ተሳትፎ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተለይም ለቀረበው ጥሪ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለሐይቅ ዳርቻው ልማት ድጋፍ ያደረጉ አካላት ምስጋና እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ የህዝብና የመንግሥት የጋራ ራዕይ ማሳያ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባ ጥራቱ፣ ለሥራው የተበረከተው የገንዘብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ ለታለመለት አላማ ውሎ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

እስካሁን ድጋፋቸውን ገቢ ላደረጉት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ ቃል ገብተው እስካሁን ያላስገቡ ወገኖች ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቃላቸውን ፈጽመው የልማቱ አካል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

አዲሱ የ2019 ዓ.ም የጀመሩትን የልማት ጉዞ የሚያፋጥኑበት፣ አዳዲስ እቅዶችን ወደ ተግባር የሚቀይሩበትና የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግቡበት ዓመት እንደሚሆንም ከንቲባው አብራርተዋል።
#hawassa #hawassalake #ethiopianews #development #infrastructure #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

27 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.