Logo
Getu Temesgen
"የቴክኖሎጂ ዕድገት ለሰብአዊ ክብርና ለፍትህ ልንጠቀምበት ይገባል!" ካርዲናል አቡነ ብርሀነየሱስ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለ2019 አዲሱ ዓመት የአንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈች

የቀድሞ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሳትና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል የአንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ብጹዕነታቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ አዲሱ ዓመት የተጣሉ የሚታረቁበትና ይቅር የሚባባሉበት፣ ፍጹም ሰላምና ፍቅር የሚሰፍንበት ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የዕርቅና የምሕረት ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን የገለጹት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ፣ ሕዝቡ ላለፉት መልካም ነገሮች ሁሉ አምላክን እንዲያመሰግን፣ ጥፋቶችና ኃጢአቶች ደግሞ በትሕትና ይቅርታንና ምሕረትን እንዲለምን ጥሪ አቅርበዋል።

የሰው ልጅ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ዕድገትና እውቀት ለሰብዓዊ ክብርና ለፍትሕ ማሰፈኛ ሊጠቀምበት እንደሚገባም በማሳሰብ፣ የሰውን ልጅ ክብርና ሰብዓዊነት የሚረግጡ መሣሪያዎችንና ተግባራትን ማከናወን ስህተት መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ ሕመምተኞችን፣ የታሰሩትንና በጭንቀት ውስጥ ያሉትን ወገኖች በማሰብና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #ethiopiannewyear #ethiopiancatholic

27 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.