Logo
FastMereja
በከተማዋ የምገባ ፕሮግራም በየአመቱ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እየተደረገ መሆኑን የምገባ ኤጀንሲ አስታወቀ

👉በየእለቱ ከ41 ሺ በላይ አቅመ ደካሞች ትኩስ ምግብ እየቀረበላቸው ነው ተብሏል

👉41 ባለሃብቶች በመርሃ ግብሩ እተሳተፉ ነው

👉ሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለማህበራዊ
ሃላፊነት በየአመቱ ከ40 ሚሊየን ብር ያላነሰ ገንዘብ ወጪ እንደሚያድ አስታውቋል

የአዲስ አበባ ምገባ ኤጀንሲ ከ41 ሺ በላይ ለሚሆኑ አዛውንቶች እና አቅመ ደካሞች በከተማው በሚገኙ 31 የምገባ ማእከላት በየቀኑ ምግብ እያቀረበ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ስንታየሁ ማሞ በዛሬው እለት በተስፋ ብርሃን ቁጥር 14 የምገባ ማእከል ለበአል መዋያ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ በተደረገበት ወቅት እንደተናገሩት በከንቲባ አዳነች አበቤ ሃሳብ አመንጪነት እና ክትትል የከተማ አስተዳደሩ አቅም የሌላቸው አዛውንቶችን በየእለቱ እየመገበ ነው።

በዚህም በከተማው ውስጥ በልበ ቀና ባለሃብቶች በተገነቡ እና በሚተዳደሩ 31 የምገባ ማእከላት በጠቅላላው በየእለቱ ከ 41 ሺ በላይ አቅመ ደካሞች ትኩስ ምግብ እየቀረበላቸው ይገኛል ብለዋል፡፡

እንደ ኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ገለፃ በምገባ እና ተያያዥ ስራዎች በየአመቱ ከ 5 ቢሊየን ብር በላይ በዚህ ድጋፍ በሚሳተፉ 41 ባለሃብቶች ወጪ እንደሚደረግ ነው የገለፁት፡፡

የአዲስ አመት በአልን አስመልክቶ በሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተገንብቶ በየእለቱ 300 አካባቢ አቅመ ደካማ አዛውንቶች በየእለቱ ምገባ የሚደረግበት ኮተቤ አካባቢ የሚገኘው የተስፋ ብርሃን ቁጥር 14 ምገባ ማእከል ላይ በተደረገው የበአል መዋያ ድጋፍ መርሃ ግብር ለ 250 አዛውንቶች የዶሮ፣ ዘይት፣ ሽንኩርት እና ዱቄት ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ላለፉት 25 አመታት በትምህርት፣ ድጋፍ ለሚሹ ህፃናት፣ አዛውንቶች እንዲሁም የጤና መታወክ ለገጠማቸው እና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እንደሚወጣ ነው በመድረኩ የተገለፀው፡፡

በተጨማሪም በመንግስት እና የማህበረሰብ አካላት በሚደረግለት ጥሪ ለሰው ሰራሽ ሆነ የተፈጥሮ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት የበኩሉን እየተጫወተ መሆኑን በመድረኩ የተገኙት ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ገልፀዋል፡፡

ለዚህም በጎ አላማ በስሩ በሚገኙ ኩባንያዎች አማካኝነት በየአመቱ ከ43 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርግ ነው የታወቀው፡፡

ሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከሚያደርጋቸው እጅግ በርካታ የህበረተሰብ ተኮር ድጋፎች እና መደጋገፎች መካከል አንደኛው የሆነውን የአውዳመት ማእድ ማጋራት መርሃ ግብር ዿግሜ 5 ቀን 2018 ዓም ባከናወነበት ወቅት የተገኙት የኩባንያው ከፍተኛ ሃላፊዎች ይህ ድጋፍ ለዘመናት ከኩባንያው ጋር የኖረ ነው ብለዋል፡፡

ሴንቸሪ ባስገነባው የምገባ መአከል በተደረገው ድጋፍ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ተወካይ እንዲሁም የከተማዋ ምገባ ኤጀንሲ አመራር እና የየካ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

“መስጠት ያስደስታል፣” ያሉት የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር “ሌሎችም ይህን አርአያ ተከተሉ፣” ሲሉ ሴንቸሪ እያደረገ ያለውን ሰው ተኮር ስራ በምሳሌነት በመጥቀስ ጥሪ ያቀረቡት።

በመድረኩ የሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከፍተኛ የስራ ሃላፉ የሆኑት አቶ ግርማ አዲስ መደጋገፍ የቆየ የኩባንያው ባህል መሆኑን ጠቅሰው።

ይህንኑ የማህበራዊ ሃላፊነት ስራ በተዋቀረ መልኩ ለማከናወን ፋውንዴሽን ለማቆም ስራው መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

እኛ የገንዘብ ወይም የአይነት ድጋፍ ማድረግ ብቻ ላይ አልተወሰንም ያሉት አቶ ግርማ ይልቁንም የተለያዩ በጎ ስራ ውስጥ የሚገኙ ተቋማት ውስጥ በቦርድ እና ሞያዊ ምክር በመሳተፍ ውጤታማ እንዲሆኑ የበኩላችንን እገዛ በማድረግ ጭምር እንሳተፋለን ሲሉ አክለዋል።

በሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የእርዳታ ማስተባበሪያ ዴስክ ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ራሄል ተስፋማርያም በበኩላቸው በኩባንያው ስር የሚገኙ ድርጅቶች ላለፉት 25 አመታት በበጎ ስራ እየተሳተፉ ቆይተዋል ብለው።

በተለየ በአዲስ አበባ፣ ቢሾፍቱ፣ ደብረ ብርሃን እና ሌሎች ለተሞች በቋሚነት ድጋፍ ለሚያደርጉ ከ10 ላላነሱ ተቋማት በቋሚነት በጀት በመያዝ የገንዘብ እና የአመራር ምክር ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

አክለውም ድጋፉ በዋናነት እገዛ ለሚሹ ህፃናት፣ አረጋውያን እንዲሁም ሴቶች ትኩረት እንደሚሰጥ አስታውሰዋል።

ትምህርት ቤት ገንብቶ ማስረከብ ብቻ ሳይሆን ለተማሪዎች ቋሚ የትምህርት መርጃ መሳሪያ እና ዩኒፎርም እንደሚቀርብ አስታውሰዋል።

በተጨማሪ የላቀ ውጤት ላላቸው ተማሪዎች በአመት ሁለቴ የማነቃቂያ ሽልማት በማበርከት ቤተሰባዊ አጋርነት የሚከናወን መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተመሳሳይ መስራት እና መለወጥ ለሚቸሉ ሴቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ በማቅረብ ሰርተው ራሳቸውን እንዲችሉ እና ቋሚ የገቢ ምንጭ እንዲኖራቸው ድጋፍ እንደሚደረግ ነው የጠቀሱት፡፡

ኩባንያው በእርዳታ ድርጅቶች አማካኝነት ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ ለበርካታ ዜጓች በቋሚነት ድጋፍ እንደሚደረግ ነው አስተባባሪዋ የገለፁት።

ከበአል ጋር በተያያዘም እንደ ባህሉና ወጉ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በተለያየ አጋጣሚ የበኩሉን ሲጫወት ነው የቆየው።SECO የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
#centuryinvestmentgroup #steelyrmi #etbusinessview #ቅዳሜገበያ #csr

27 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.