Logo
Getu Temesgen
የፕሬዚዳንቱ ልጅ የቱርክ ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዙ
#ethiopia | ​የኡጋንዳ ኃይል ዋና አዛዥ እና የፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ የሆኑት ሙሁዚ ካይነሩጋባ በሀገሪቱ የሚኖሩ የቱርክ ዜጎች በአስቸኳይ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ በቶሎ እንዲወጡ ጥሪ አቀረቡ።

ጄነራሉ በኤክስ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ከቱርክ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ማቋረጣቸውን የገለጹ ሲሆን በመስከረም 18 ቀን በካምፓላ በሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ ፊት ለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ አስተላላፈዋል።

​በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈጠረው ውጥረት ዋነኛ መንስኤ በቱርክ የሚኖረውና የኡጋንዳ መንግሥትን አብዝቶ የሚተቸው ፍሬድ ሉምቡዬ የተባለው ብሎገር ጉዳይ እንደሆነ ተመልክቷል።

ሙሁዚ ካይነሩጋባ ቀደም ሲል የቱርክ ባለስልጣናት ይህንን ተቃዋሚ አሳልፈው እንዲሰጧቸው ወይም ከሀገራቸው እንዲያባርሩት አጥብቀው ሲጠይቁ የቆዩ ቢሆንም ጥያቄያቸው ባለመመለሱ ምክንያት እርምጃው ወደ ጥብቅ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት አድጓል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

28 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.