ግብ ጠባቂው ንጉሣዊ ዙፋን ሊደፋ ነው!
#ethiopia | በእንግሊዝ ሦስተኛ ዲቪዚዮን በመጫወት ላይ የሚገኘው የ36 አመቱ ግብ ጠባቂ በኡጋንዳ የሚገኘውን የቶሮ ንጉሣዊ ዙፋን ለመረከብ ተመርጧል።
ከሰሞኑ በ34 አመታቻው ህይወታቸው ያለፈው የቀድሞ የቶሮ ንጉሥ የነበሩት ንጉሥ ኦዮ ኒዪምባ 4ኛ የሚተካ ይሆናል።
የሟቹ ንጉስ የአጎት ልጅ የሆነው የ36 አመቱ ጆርጅ ዴስሞንድ ካሙራሲ የንጉስነት ቦታውን እንዲረከብ መመረጡ ታውቋል።
የቶሮ ንጉሣዊ የዙፋን ተከታይ ኮሚቴ ባካሄደው ድምፅ አሰጣጥ ካሙራሲ ከተሰጡት 18 ድምፆች 15ቱን በማግኘት አዲሱ ንጉሥ እንዲሆን በኮሚቴው ተመርጧል።
ካሙራሲ የቀድሞው ንጉሥ ጆርጅ ሩኪዲ 3ኛ የልጅ ልጅ እና የሟቹ ንጉሥ ኦዮ የአጎት ልጅ ነው።
ካሙራሲ የንጉሥነት ዘውዱን ለመደፋትና ባህላዊ ኃላፊነቱን ለመረከብ የእግር ኳስ ሕይወቱን አቋርጦ ወደ ምዕራብ ኡጋንዳ ለመጓዝ በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #uganda #toorokingdom #georgekamurasi #footballnews #africanews

29 days ago