Logo
SeledaPost
ትራምፕ ካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ ግሪንላንድ፣ አይስላንድ እና ሌሎችንም ግዛቶች ከአሜሪካ ጋር አቀላቅሎ የሚያሳይ ካርታ አጋሩ፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን አሜሪካን እና አቅራቢያ የሚገኙ ግዛቶችን በአሜሪካ ሰንደቅ  ዓላማ ስር አጠቃሎ የሚያሳይ ካርታ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ አጋርተዋል።

ይህም አዘጋጅተው ያቀረቧቸውን ካርታዎች እና የጂኦግራፊያዊ ስሞች ለውጦችን ለፖለቲካዊ መልእክት ማስተላለፊያነት የመጠቀም አካሄዳቸው መቀጠሉን ያሳያል።ያለ ምንም ተጨማሪ ማብራሪያ የተለቀቀው ይህ ምስል፤ አሜሪካን ጨምሮ ሰፊውን የካናዳ፣ የግሪንላንድ እና የሜክሲኮ ግዛቶች በአሜሪካ ባንዲራ ተሸፍነው ያሳያል።

አርክቲክ ቱደይ እንዳስነበበው፤ ይህ ምስል ማዕከላዊ አሜሪካን፣ ካሪቢያንን እና አይስላንድን ያካተተ ሲሆን፤ መላው ቀጠናም የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ መንግስት በሚል ተሰይሟል።

በምስሉ ላይ የአይስላንድ መካተት ልዩ ትኩረትን ስቧል። አርክቲክ ቱደይ ቀደም ሲል በትራምፕ እና በደጋፊዎቻቸው ይሰራጩ የነበሩ ካርታዎች ግሪንላንድ፣ ካናዳ እና ቬንዙዌላን ያካተቱ እንደነበሩ፣ አይስላንድ ግን ከዚህ ቀደም በዚህ መልኩ ተካታ እንደማታውቅ ገልጿል።

Seledadotio
Seledadotio
28 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.