Logo
Getu Temesgen
የሰው ልጅ ይሞታል እነሱ ግን "የማይሞቱ" ሰዎቻችን ናቸው!
#ethiopia | ጣሊያኖች አንድ ሰው ለሀገሩ እና ለዓለም ባበረከተው ድንቅ ስራ ምክንያት አሻራው ትውልድ ተሻጋሪ ሲሆን “የማይሞት ሰው” በማለት ያከብሩታል።

በጣሊያን ባህልና ታሪክ ውስጥ ለሀገራቸው እንዲሁም ለዓለም ታላቅ ውርስ ጥበብ እና እውቀት አበርክተው ያለፉ ታላላቅ ሰዎች “የማይሞቱ” ተብለው በክብር ስም ይጠራሉ።

እነዚህ ሰዎች በስጋ ቢለዩም፣ ያከናወኗቸው አስደናቂ ስራዎች ትውልድ ተሻጋሪ በመሆናቸው እስከዛሬ ድረስ ስማቸው ሳይደብዝዝ ህያው ሆኖ ይኖራል።

በዓለም እና በጣሊያን ታሪክ ውስጥ ይህንን “የማይሞት” የሚል የክብር ስም ካተረፉ ታላላቅ ሰዎች መካከል እነዚህ ይገኙበታል።

የሞናሊዛ (Mona Lisa) ስዕል ፈጣሪ፣ ድንቅ መሃንዲስ እና የህክምና ሳይንስ አቅኚ የነበረው ሊዮናርዶ ዳቪንቺ በጥበቡ ዓለምን ያሰደመመ ምሁር ይህንን የክብር ስም የተሰጠው ሰው ነው።

የዘመናዊው የጣሊያን ቋንቋ አባት እና የዓለም የስነ ጽሁፍ ሀብት የሆነው “ዲቫይን ኮሜዲ” ደራሲ ዳንቴ አሊጊየር ሌላኛው ነው።

የቫቲካኑን ሲስቲን ቻፔል ድንቅ ስዕሎች እና የዳዊትን ሀውልት ያነጸው ወደር የሌለው የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያው ሚካኤል አንጀሎ የክብር ስሙን ከተቀዳጁት ሰዎች መካከል ይገኝበታል።

የዘመናዊ ኮስሞሎጂ እና የፊዚክስ አባት የሰማይ አካላትን በቴሌስኮፕ በመመርመር የዓለምን አስተሳሰብ የለወጠው ታላቁ ሳይንቲስት ጋሊሊዮ ጋሊሊም የክብር ስሙ የተሰጠው ሰው ነው።

እንደዚሁም በጣሊያን እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ እጅግ ስኬታማ የነበረውን የ1980ዎቹ መጨረሻ እና የ1990ዎቹ መጀመሪያ የኤሲ ሚላን ቡድን አሰልጣኝ አሪጎ ሳኪ እና ተጫዋቾቹን እንደ ማልዲኒ ባሬሲና ቫን ባስተን ያሉ ተጫዋቾችም ጣሊያኖች "የማይሞቱት"ሰዎች ብለው ይጠሯቸዋል።

“ሰው ይሞታል፤ ስራ እና አሻራ ግን ለዘላለም ህያው ሆኖ ይኖራል!”

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #italian #scientists #gliimmortali #history #inspiration #knowledge

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.