Logo
Getu Temesgen
“የአፍሪካ ዕድገት በእርዳታ ሳይሆን በሥራ ፈጠራ ነው የሚረጋገጠው!”
#ethiopia | ናይጄርያዊው ባለሀብት ቶኒ ኤሉሜሉ የውጭ እርዳታ ጊዜያዊ ችግራችንን ቢቀርፍም የአህጉሪቱን ዘላቂ እድገት የሚያረጋግጡት ግን የራሳችን ሥራ ፈጣሪዎች ናቸው ብለዋል።

ቶኒ ኤሉሜሉ የአፍሪካን ኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠን ለሥራ ፈጠራ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ጥሪ አቀረቡ።

ሥራ ፈጣሪዎች የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን መገንባትና
ለማህበረሰቡ ፈተና የሆኑ ችግሮች መፍትሔ ማበጀት አለባቸው ብለዋል።

እንዲሁም በአፍሪካ እያደገ የመጣውን የህዝብ ቁጥርና የተፈጥሮ ሀብት ወደ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድል መለወጥ ይችላሉ ብለዋል።

“አፍሪካ እርዳታ አያስፈልጋትም አፍሪካ የሚያስፈልጋት ሥራ ፈጣሪዎች ናቸው" ብለዋል።

አፍሪካውያን በኢንቨስትመንት በፈጠራና በንግድ ሥራዎች አማካኝነት የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ በመቅረፅ ረገድ ግንባር ቀደም ሚና መጫወት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #africa #entrepreneurship #africapitalism #donation

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.